ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት እንደተወሰደ አልታወቀም

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት እንደተወሰደ አልታወቀም

ቤተሰቦቹ ፍለጋ ላይ ናቸው!
ማእከላዊም ሆነ ሌሎች እስር ቤቶች አልተገኘም!

/Ethiopia Nege/:- በተለያዩ ድፍረትና እውነት ያዘሉ ጽሁፎቹ የሚታወቀው የቀድሞዋ ፋክት ጋዜጣ ባለቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለረጅም ጊዜ ታስሮ የነበረበት የዝዋይ እስር ቤት ውስጥ እንደማይገኝና የት እንደደረሰ እንደማይታወቅ ይፋ ሆነ፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ከጥቅምት 3,2007 ዓም ጀምሮ ከሁለት አመት በላይ በእስር ሲቆይ በቤተስብ እንዳይጎበኝ እስከመከልከል የደረሰና የተለያዩ ተጽእኖዎች ይደርሱበት እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በአመክሮ የመፈቻ ሰአቱን በይፋ የተከለከለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከኅዳር 28/09 ጀምሮ ላለፉት ተከታታይ ቀናት የት እንዳደረሱት ካለመታወቁም በላይ ቤተሰብቹ የዝዋይ እስርቤት ሃላፊዎች ‘ተመስገን እዚህ የለም ግቢውን ለቃችሁ ውጡ’ መባላቸውን ገልጸዋል፡፡

የጋዜጠኛ ተመስገን ቤተሰቦች አዲስ አበባ የሚገኙትን የቃሊቲ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች ጨምሮ የሸዋሮቢት እስር ቤትና የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ለማጣራት ቢሞክሩም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ ተመስገን የት እንዳለ የሚያሳይ ምንም አይነት ፍንጭ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ በፌስ ቡክ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

ተመስገን ደሳለኝ በየሳምንቱ በተለያዩ ጋዜጦቹና ድረ ገጽች ላይ በሚያቀርባቸው ጽሁፎቹ በአገዛዙ የደህንነት ሰዎች ሲታፈን፡ ሲዋከብና ሲታሰው የነበረ እንደመሆኑ መጠን በአንጻሩ የፈራ ይመለስና በሌሎች አጫጭር ጽሁፎቹ የበርካታ አንባቢያንን ቀልብ ስቦ እንደነበር የሚዘነጋ አይደልም፡፡

/Ethiopia Nege Dicember 9,2016/

LEAVE A REPLY