ስለ አማራ መደራጀት ግራ ለገባቸው! ምላሽ ለተክለሚካኤል አበበ /አቻምየለህ ታምሩ/

ስለ አማራ መደራጀት ግራ ለገባቸው! ምላሽ ለተክለሚካኤል አበበ /አቻምየለህ ታምሩ/

አንዳንዶች በነጻነትና አማራጭ በሞላበት ካናዳና አሜሪካ እየኖሩ በፋሽስት ወያኔዋ ኢትዮጵያ ህልውናው እየጠፋ ያለው አማራ በአማራነት መደራጀቱ የምርጫ ጉዳይ እየመሰላቸው አማራው የተጋረጠበትን የፈጽሞ መጥፋት አደጋ አለመገንዘባቸውና መሬት ላይ ካለው እውነታ ፈጽመው የተለዩ መሆናቸውን በአደባባይ ይነግሩናል።

አማራ ለምን ይደራጃል? የሚለውን ጉዳይ ሳይፈትሹ «አማራው ሲጠቃ የኖረው በኢትዮጵያዊነት ነው» ይሉናል። ሁሉ ነገር ቢቀር እንዴት ወያኔ በታስሳህ ወር 1968 ዓ.ም. የጻፈውን ማኒፌስቶ ያነበበ ሰው እንዴት ይህንን በድፍረት ይናገራል? ኦነግም ሆነ ወያኔ እንዲሁም የተቀሩት የጥላቻ ድርጅቶች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የጠሉት አማራን ስለሚጠሉ ብቻ ነው። ይህንን ራሳቸው ነግረውናል! 

ወያኔ የፈጠረው የትግሬ ማንነት ከአማራ ጥላቻ በስተቀር substance የለውም። ኦነግ የፈጠረው ኦሮሞነት ከአማራና ጥላቻ በስተቀር substance የለውም። እነዚህ ሁለቱ የእፉኝት ድርጅቶች ፖለቲካቸው የአማራ የዘር ማጥፋት ስለሆነ ህልማቸው አማራን አጥፍተው የራሳቸውን መንግስት መመስረት ነው። ወያኔም ሆነ ኦነግ በፍኖተ መርሀቸው እንደ ግብ የራስን አገር መመስረትን ሲያስቀምጡ እንደ ስልት የያዙት ደግሞ አማራን ማጥፋት ነው።

ባጭሩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአማራ ጥላቻ ነው። ይህንን ማየት ያልቻሉ አማራጭ በሞላበት አለም የሚኖሩት እነ ተክለሚካኤል አበበ ግን ቶሮንቶ ውስጥ ከሚገኙት ከላሊበላ፣ ከሳባ ወይንም ከሉሲ ሬስቶራንቶች ራት ለመመገብ የሚደላው የትኛውን ሬስቶራት ምርጫችን ብናደርግ ነው አይነት አማራጭ ላይ ቁጭ ብለው የአማራን መደራጀት ጉዳይ የሬስቶራንት ወይንም የምግብ ሜኑ ምርጫ ጉዳይ አድርገውት አረፉ። ይህ ተክለሚካኤል አበበ ስለአማራ መደራጀት ጉዳይ የጻፈው ድርሳን የፈረንሳዩን የንጉስ ሌውስ XVI ባለቤት የነበረችው ንግስት ማሪያ አንቶኔ ዳቦ አጥተው በድህነት የዳሸቁ እና በረሀብ እየሞቱ የነበሩትን የፈረንሳይ አርሶ አደሮች «ለምን ኬክ አይበሉም» ያለችውን የቅምጥል ልጅ ምርጫ ያስተውሰኛል። የኛው አቶ አሰፋ ጫቦም እንዲህ አይነቱን የሩቅ ድፍረት «መትፋት ያስነውራል» ይሉታል! በጽሁፉ እንዳየሁት ተክለሚካኤል አበበ ከአማራ ችግር እጅግ የራቀ ይመስላል። ለነገሩ «ከአይን የራቀ ከልብ ይርቃል» አይደል ነገሩ።

ተክለሚካኤል አበበ ቀጥል ያደርግና «ወልቃይት የጎንደር መሆኑን ያጸደቅን እለት፤ አዲስ አበባንም የዚህ ብሄር ነው የሚለውን አስተሳሰብ ልናጸድቅ ነው» ይለናል! ተክለሚካኤል «የዚህ ብሔር» ለማለት የፈለገው የኦሮሞ ለማለት ፈልጎ መሰለኝ። ተክለሚካኤል በወያኔ ዘመን ቆሞ ላይ ይህንን ሲናገር ወልቃይትም ሆነ አዲስ አበባ ታሪክ እንዳላቸው የዘነጋው ይመስላል። የአማራ ክልል ኢትዮጵያ ናት። አማራ የሚደራጀው ወያኔ ባባጀለት አጥር ለመታገት ሳይሆን በሰፊዋ ኢትዮጵያ ያለ ገደብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን እኩል እንደሰው ተከብሮ ለመኖር ነው። የአማራ መደራጀት ግብ ይህ ነው። ከዚህ የተለየ ፍቺም ሆነ ትርጉም የለውም።

ስለ እውነት ተክለሚካኤል ስለአማራ መደራጀት አላማ ሲጻፍ ከከረመው አንጻር የመነሻ ያህል እንኳ የገባው አልመሰለኝም። አማራው ከተደራጀ ለምን ቦረና ይሄዳል አይነት ጥያቄ ያነሳል። ተክለሚካኤል አማራ ዛሬ የሚደራጀው ከሶስት ሺህ ዘመናት በላይ በደምና በአጥንቱ ዳር ድንበሯ ታፍሮ ሉዓላዊነቷ ተከብሮ በኖረችው ባባቶቹ አገር በቦረና የአገሩ ባለቤት ሆኖ ሊኖር ባለመቻሉ መሆኑ የገባው አይመስልም። ልጅ ተክሌ አማራ የሚደራጀው እንደ ኦነግና ወያኔ ዘረኛ ለመሆን አይደለም። አማራ የሚደራጀው የተጋረጠበትን አደጋ ተቋቁሞ በሰፊው ያባቶቹ አገር የአገሩ ባለቤት ሆኖ ለመኖር የሚያስችለውን አቅም ለመፍጠር ነው። የአማራ የሚደራጀው ስለዚህ ቅዱስ ተግባር ነው!

LEAVE A REPLY