የሀወሓት ኢህአደግ ጥልቂ ተሀድሶ /አስገደ ገብረስላሴ – መቀሌ/

የሀወሓት ኢህአደግ ጥልቂ ተሀድሶ /አስገደ ገብረስላሴ – መቀሌ/

የሀወሓት ኢህአደግ ጥልቂ ተሀድሶ እንደ የኢሊኖደረቅ
ነፋስ ነፍሶ ቀረ!!
የህወሓት ኢህአደግ ፓርቲና እሱ የሚመራው መንግስት በለፉት 25 አመታት ምንም እንኳን ደርግን አስወግዶ በወቀቱ ድህና የሚባል ህገመንግስት ተረቆ ከነቡዙ ሽግሮቹ በተወካዮች ምክርቤት አጸድቆ ካለፉት የዘውዳዊ ስርአት እና የደርግ ስርአት የተሻለ ህገመንግስት ተብሎ ከዛ በፊት ያልነበሩ መብቶች የመተግበር ምልክቶች ታይተው ነበር።

ሆኖም ግን ህወሀት ኢህአደግ በነጻ የሆኑ ሙሁራን የተረቀቀና የጸደቀ ህገመንግስት ቀስ በቀስ እየናዱት በሚሊዮኖች ታጋይ ዜጎች መስዋእት ፣አካል መጉደል የተረጋገጡ መብቶች በመንጠቅ አብዛኞቹ በህገመንግስት የተረጋገጡ ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተሸረሸሩ ።ለህወሓት ኢህአደግ ጠንክረው የሚቃወሙ ፓለቲካ ፓርቲዏች ልዩነቱ በሰላማዊ መንገድ በክብ ጠረቤዛ በውይይት እንደመፍታት ለሚነሱ ጥያቄዏች በአፈሙዝ ጠበንጃ መፍታት ተያያዘው።

የህወሓት ኢህአደግ አመራር ደርግን አስወግጄ በመቃብሩ ዲሞክራሲያዊ ስርአት እንዲያብብ አደርጋለሁ በማለት ቃለመሀላ ሲፈጽም የነበረው ሳየውል ሳያድር እየካደ መጣ። ህወሓት ኢህአደግ በውስጠ ፓርትና በትግራይ ህዝብ ይነሱ የነበሩ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዏች በማፈን ድብቅና ግልጽ እሱር ቤቶች በማስፋፋት ቡዙ ወገኖች ያለፍርድ ቤት ውሳነ በአስርሽ የሚቆጠሩ ታጋዮች፣ ነዋሪ ህዝብ ታሰሩ፣ ተባረሩ፣ የህወሓት አማራር ከእንግዲህ ወዲህ በረሀ እንደነበረ ጥራዝ ነጠቅ መብት የለም ። አፋችሁ ያዙ አለ ።በቃ ልክ እንደደርግ አንባገነን እየሆነ መጣ።
የስልጣኑ መዋቅር በዘመድ፣ በጋብቻ፣ በጓደኝነት ፣ በአውራጃ ፣በጎጥ የተሳሰረ የአገዛዙ መዋቅር አጠናክሮ ዘረጋ።

በሌላ በኩል የህወሓት አማራር እሱ የሰራቸው ፓርቲዏች በህወሓት አስተሳሰብና ፓሊሲ እንዲዋቀሩ ተደረገ። ህወሓት ከሰራቸው ፓርቲዏች ውጭ፣ ነጻ ሀሳብ ይዞ በራሱ መስመር፣ በራሱ ፖሊሲ፣ ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ይሁን ግለ ሰው እምቢ ላለ ሰው ጥይት አጉርሰው ተባለ። ከ70 በላይ የግል ፕሬሶች ቀስበቀስ ተዘጉ ። ጋዜጦኞች፣ አሳታሚዏች ታሰሩ ካገር ውጭ ተሰደዱ ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዏች ፣አባሎቻቸው ፣ደጋፊዏቻቸው በውሀ ቀጠነ ታሰሩ ፣ተገደሉ ቆሰሉ ፣ ካገር ውጭ ለስደት ተበታተኑ።
ህወሓት ኢህአደግ አመራርና ካድሬዏቹ ፣ሸሪኮቹ ከላይ የተዘረዘሩት አፈናዏች ከወሰደ በኃላ የበላይነቱ ከአረጋገጠ የሀገራችን የኢኮኖሚ አውታሮች በመቆጣጠር፣ የሀገራችን ተሽጠው ዋጋ ሊያወጡ የሚችሉ ቁልፍ የንግድ ማእከላት ሆነው የገንዘብ ምንጭ የሚሆኑ መሬት በመውረር፣ የትራንስፖርት፣ የባንክ ፣የእንሹራንስ፣ የእንድስትሪ፣ የትሪዙም ፣ የህርሻ ኩባንያዏች በግለሰውና በቡዱን ተቆጣጥረው በመያዝ፣ እንዲሁም በመላው ሀገራችን ያሉ ምርጥ የእርሻ ፣የቤት መስርያ ቦታዏች ተቆጣጥረው ሀገራችን የጥቂት የመንግስት ባለስልጣናት እና የልጆቻቸው፡ የዘመድ አዝማድ ፣የሸሪኮቻቸው መፈንጫ አድርገዋታል።
የመንግስት ስልጣናቸው በመጠቀም እቺ ሀገር የሙሱና እና የክራይ ሰብሳቢዏች በመንግስት ስልጣን የባለጉ፣ ሀብታችን ተወረዋል። ከላይ የዘረዘርኳቸው ቡልሽው አሰራር የጀመረውና የተስፋፋው በዘመነ ስልጣን ጠቅላይ ምንስቴር መለስ ዜናዊ ነበር ስር የሰደደው። በወቅቱ ሁኔታው ሲባባስ መላው ህዝባችን ለስርአቱ ተቃውሞ በማሳያታቸው ያልተመጣጠነ ንሮ በመስፋፋቱ ፣የስራ አጥነት፣ አድልዏ የፈጠረው የህዝብ ተቃውሞ በመቀጣጠሉ ፣ የፍትህና የመልካም አሰተዳደር እጦት በመባባሱ የመለስ ስርአት እና መዋቅሩ ተነቃነቀ።

በዛንጊዜ የህወሓት ኢህአደግ አመራር ከበረሀ ይዞት የመጣ ጸረዲሞክራሲ ተፈጥሮ እና ባህሪ ሲጨንቀው ተሀድሶ ወይ ድርጅታዊ ጥራት በሚል እንደ ማብረጃ ሲጠቀምበት የነበረ የጸረ ዲሞክራሲ የግርጭት አፈታት ይከተል የነበረው ።መለስም በ1993 ዓ ም ታድሶ በሚል ለጥልቅ ብልሽውነታቸው ለመደበቅ ተሀድሰናል በሚል በማጭበርበር ፣ሙሱና ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ፣ በመንግስት ስልጣን በመጠቀም የህዝብና የመንግስት ሀብት ምዝበራ እናጠፋለን በማለት ለ15 አመት ሲያጭበረበሩን ነረዋል ። በ15 አመት መሉ ግን የተሻሻለ ነገር አልነበረም። በዛን ጊዜም ተሀድሰው እንደዘንድረው በጥልቅ ተሀድሶ እንደ እሊኖ ነፋስ ነፍሶ ነበር የቀረው።

መለስ ካለፈም በኃላም ጠቅላይ ምኒስቴር ሀይለማርያም የመለስ ሌጋሲ እከተላለሁ ፣አገራችን በመለስ መርህ አደገች ተመነደገች እያለ ከርሞው ዛሬ ከ15 አመት በኃላ፣ ያለፈው 15 አመት ተሀድሶ አልሰራም፣ እንዳውም ሀገራችን ከቤተመንግስት እስከ ቀበሌ ያለው የኢህአደግ እና መዋቅሩ እሱ የሚመራው መንግስት ባለስልጣኖቻችን ለግል ጥቅማቸው በማዋል ከቤተመንግስት እስከ ቀበሌ የደላዮችና ሌቦች መዋቅር በመዘርጋት ሀገራችን የመንግስትን ስልጣናቸው በመጠቀም በሙሶኞች እና ኪራይ ሰብሳቢነት ተወራለች። በመሆኑ ሙሶኞችና ኪራይ ሰብሳቢዏች ከነሸሪኮቻቸው እና ደላዮቻቸው ከቤተመንግስታችን እስከቀበሌ የለው በመጠራረግ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ቱቱላቸውን ሲነፉ ከርመዋል።
እጅጉን ለመላው ህዝባችን አግራሞት የፈጠረው ደግሞ ሀቀኞች ነን ብለው ለማስመሰል ከራሳቸው ጠ/ም/ ሀይለማሪያም ደሳለይ እስከ ቀቤሌ ያሉ ባለስልጣናት የህዝብና የመንግስት ሀብት ወረው ደበቀው ሲያበቁ በተለብዝን መስኮት ብቅ እያሉ ፣ሙሶኞች ኪራይሰብሳቢዏች አጋልጠን ለፍርድ እናቀርባቸው አለን እያሉ አመት ሙሉ ሲያደነቁሩን ከርመዋል። ሁሉም ሌቦች በመሆናቸው ከአመት በላይ የመንግስት ገንዘብ ከአቅማቸው በላይ አበል እየተከፈላቸው፣ የኢሀአደግ ምክርቤት፣ ስራ አሰፈጻሚ ፣ የፓርቲዏች ማእከላይ ኮሚቴ፣ የከፍተኛ፣ መካከለኛ ፣የዝቅተኛ፣ አመራር መላው የመንግስት ፣ሰራተኛ፣ አስተማሪዏች፣ ተማሪዏች ፣አርሶ አደሮች፣ የከተማ ነዋሪ ህዝብ፣ የመከላከያ የፖሊስ ፣የልዩ ሀይል ወዘተ አመት ሙሉ ተሰብስበው ከርመው፣ የመንግስት ስልጣን ተጠቅመው ሀገር የወረሩ ሙሶኞች እና ኪራይሰብሳቢዏች አንድ ሰውም ለፍርድ የቀረበ ፣ የተቀጣ ሰው የለም።

እንዳውም በስብሰባው የከረሙ ድሀ ካድሬዏች እንደሚሉት ከቤተ መንግስት እስከቀቤሌ ያሉ ባለስልጣኖች ልጆቻቸው ሸሪኮቻቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ሁሉም ሌቦች ስለሆኑ ፣በሀገር ደረጃ ሀብት ስለወረርን ለዛሬ ተቻችለን እንለፈው ከእንግዲህ ወዲህ ከስርቆት እንቆጠብ ብለው ታርቀው እንደወጡ ተነግሯል። በተለይ የህወሓትና የበአዴን ማእከላይ ኮሚቴ ግምገማ ማን ለማን መታ የሚለው በፉኩክር እንዳልተጋለለጡ በግልጽ እየተነገረ ነው። የዘንድሮ የህወሓት ኢህአደግ ያለመገላለጥና ያለመማታት የወሰኑ መሆናቸው መራጋገጫ ደግሞ እነዛ አገር አጥፊዏች ተብለው የተጠረጠሩ ባለስልጣናት ከነበሩበት ስልጣን ወርደው የመከሰስ መብት ተነስቶ እንደመከሰስ በአንጻሩ ባገር ውስጥ የበለጠ ስራ ይሰጣሉ። ቤተሰቦቻቸው ይዘው በየአገሮች በአንባሳደርነት ፣በጉዳይ አስፈጻሚነት ተመድበዋል።
ስለዚህ የህወሓት ኢህአደግ ፓርት እና እሱ እሚመራው መንግስት ድሮም ታድሶ አያውቅም የአሁኑ ጥልቅ ተሀድሶም እንደ የኢሊኖ ደረቅ ነፋስ በኖ ወሬ ሆኖ የቀረ ነው ።
4 / 4 / 2009 ዓ ም

LEAVE A REPLY