ማርሽ ቀያሪው ምሩጽ ይፍጥር በ72 ዓመቱ በሞት ተለየ

ማርሽ ቀያሪው ምሩጽ ይፍጥር በ72 ዓመቱ በሞት ተለየ

/Ethiopia Nege/፦ በአለም የአትሌቲክስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አክብሮትን በመጎናጸፍ እና ማርሽ ቀያሪው በመባል የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው የሩጫ ሰው ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር ዛሬ ሃሙስ December 23/2016 ምሽት በህክምና ሲረዳ በነበረበት

ቶሮንቶ ካናዳ ማረፉን ለማወቅ ችለናል።

ዝነኛው የሩጫ ሰው ምሩጽ በ1973 ሌጎስ ውስጥ በተካሄደ ውድድር በ5ሺህ እና በ10ሺህ ወርቅ በማሸነፍ፣ በ1977 በሲድልዶፍ ጀርመኒ ደግሞ በተመሳሳይ ወርቅ ወሰደው ምሩጽ በ1979 በሞንትሪያል ካናዳ 5ሺህና 10ሺህ ውድድሮችን ሳያስነካ የግሉ አድርጓቸው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

ምሩጽ ይፍጠር በ1980 በሞስኮ ኦሎምፒክ በ10ሺህ እና በ5ሺህ ኪሎ ሜትር ውድድር ከማሸነፉም በላይ በጨራረስ ስልት አንቱታን ተጎናጸፎ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በተለያዩ አለማት በተዘጋጁ ውድድሮችም በመሳተፍ ድንቅ ውጤቶችን በማስመዝገብ የሃገሩንና የመላ አፍሪካን ስም ያስጠራ እንደነበር ይታወቃል።

ምሩጽ ከወር በፊት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ሞቷል የሚል ዜና ተሰራጭቶበት እንደነበርና በአሜሪካን ድምጽ በመቅረብ በካናዳ ቶሮንቶ በህክምና ላይ እንዳለ ማስረዳቱ የሚዘነጋ አይደለም።

የምሩጽ አስከሬን ሽኝትና የመታሰቢያ ጸሎት ስነስርአት ቤተሰቦቹና ወዳጅ አድናቂዎቹ ባሉበት ቶሮንቶ በሚገኘው ቅድስት ማሪያም ካቴድራል እንደሚደረግ የደሰረሰን ማስረጃ ያስረዳል።

 ኢትዮጵያ ነገ ድረ ገጽ አባላት ለመላ ቤተሰቦቹና አድናቂዎቹ መጽናናት በመመኘት የሩጫውን ሰው ምሩጽ ይፍጠርን የሚዘክር አጭር ታሪክና የመጨረሻ ሰአት ቆይታ ያካተተ ዝግጅት ይዘን እንቀርባልን።

ማርሽ ቀያሪው በመባል የሚታወቅው የሩጫ ሰው ምሩጽ ይፍጥር ለሀገሩ በርካታ ሜዳሊያዎችን በማበርከት የሚታወቅ ሲሆን በህዝብ ዘንድ አክብሮትን ተጎናጽፎ እስከ እለተ ሞቱ ማሳለፉን የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

/Ethiopia Nege December 22, 2016/