የምሩጽ ይፈጠር አስከሬን ሽኝት በቶሮንቶ ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ተካሄደ

የምሩጽ ይፈጠር አስከሬን ሽኝት በቶሮንቶ ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ተካሄደ

/Ethiopia Nege/፦  የታላቁ ሯጭ ምሩጽ ይፍጥር አስከሬን ሽኝት ዛሬ በሽዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቹና ቤተሰቦቹ በተገኙበት በካናዳ ቶሮንቶ ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ተከናወነ።

በስፍራው በርካታ ኢትዮጵያዊያኖችና የውጭ ሃገር ዜጎች ተገኝተው ለታላቁ የሩጫ ሰው ምሩጽ ያላቸውን ክብርና አድናቆት ያሳዩ ሲሆን የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘንም ገልጸዋል።

በዚሁ ዛሬ ዲሴምበር 27/2016 በተካሄደው የአስከሬን ሽኝት ስነ ስርአት የሩጫውን ሰው የህይወት ታሪክ ያካተተ ዝግጅት ከመቅረቡም በላይ ሲቢሲ የተባለው የካናዳ ሀገር አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያዊያንና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ተገኝተው ሲዘግቡ እንደነበር ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድተዋል።

የምሩጽ ይፍጠርን አጭር የህይወት ታሪክ ለሀገሩና ለህዝቡ ያለውን ታማኝነት በማሳየት ያቀረቡት አቶ ታምሩ ተስፋዩ ሲሆኑ የቅስት ማሪያም ካቴድራል ካህን የሆኑት ዶክተር ቀሲስ መብራቱም ለመላ ቤተሰቡና ወገኖቹ አጽናኝ መልእክት አስተላልፈዋል።

      /የሽኝቱ ስነ ስርአት የቀረበውን የህይወት ታሪክ ለማዳመጥ ይህን ይጫኑ/

በፈጣን የአጨራረስ ስልቱ የሚታወቀው ምሩጽ የአስር ሺህ እና አምስት ሺህ ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮችን አጣምሮ በማሸነፍ በአለም አቀፍ እውቅናን ከማትረፉም በተጨማሪ ባለፈው መስከረም በደብረዘይት የኢሬቻ በአል ላይ ያለቁ ወገኖች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለመቃወም ኦታዋ ድረስ ለመሄድ ያቀረበው ጥያቄ በሃኪሞቹ በመከልከሉ ባይሳካለትም ‘ህዝቤ’ አለቀ በማልት ብዙ ጊዜ ሲቆጭ እንደነበርና የህዝብ ወገንተኛ ሆኖ ህይወቱን በማሳለፉም የሚታወቅ መሆኑን ቅርበት ያላቸው እማኞች ለኢትዮጵያ ነገ ገልጸዋል።

ምሩጽ በህዝብ ላይ አደጋ ሲደርስ በርካታ ጊዜ ‘ህዝቤ’ በማለት ይቆጭና ይንገበገብ እንደነበር የገለጹት እማኞች የአስከሬኑ ሽኝት በቅድስት ማርያም ካቴድራል እንዲፈጸም ከመሞቱ በፊት የህጋዊው ሲኖዶስ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን ቄስ ምሳሌ እንግዳን በማስጠራት ኑዛዜ ፈጽሞ እንደነበር ለማወቅ ችለናል።

ሽኝቱ በቶሮንቶ ተፈጸመው የሩጫ ሰው አስከሬን ወደ ሀገር ቤት የሚገባ ሲሆን በመዲናዋ አዲስ አበባ በሚደረገው የአቀባበል ስነስርአት ላይ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Ethiopia Nege December 27, 2016/

LEAVE A REPLY