የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች – መያድ ፈተናዎች በኢትዮጵያ /ከቢ.ተ አባተ/

የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች – መያድ ፈተናዎች በኢትዮጵያ /ከቢ.ተ አባተ/

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያድ) በኢትዮጵያ በብዛት የተመሰረቱት ከ1983 ጀምሮ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መንግስት ሀገሪቱን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ በህገ-መንግስቱ የመደራጀት መብት በሚፈቅደው መሰረት በተለያዩ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ፣የጤናና ስነተዋልዶ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ተመስርተው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በወቅቱ በምሳሌነት ሊጠቀስ የሚችል አለምአቀፋዊ መስፈርቶችን ያካካተ ሕገመንግስት አጽድቃ በስራ ላይ አውላ ነበር፡፡ ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ህጎቹ በአብዛኛው ተግባር ላይ የማይውሉና በተለይም ለአለምአቀፉ ማህበረሰብ ቅቡልነት ለማግኘት ብቻ ሲባል የታወጁ ናቸው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በተግባር የምትታወቀው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በመጣስ ነው፡፡ ጋዜጠኞችን፣የሲቪል ማህበራት ተወካዮችና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን በማሰር ከሚጠቀሱ ሀገራት ቀዳሚዋ በመሆን በአለም አቀፍ ድርጂቶች ጭምር ተመስክሮለታል፡፡

የመደራጀት መብት ተፈጻሚነት የሚከታተለውና የማስተዳደር ሀላፊነት የተጣለበት አካል ፍትህ ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙ አደረጃጀቶች ናቸው፡፡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያድ) በ1992 ዓ.ም ወደ ሶስት ሺህ እንደደረሱ ተገልጾ ነበር፡፡ ከፍቃድ ሰጪው በተደጋጋሚ እንደ ዲሞክራሲ መገለጫ ተደርጎ ይቀርባል፡፡ ይህም ቁጥር ከጎረቤት ኬንያ ጋር ሲነፃፀር በጣም አናሳ ነበር፡፡ በተደጋጋሚ መንግሰት ድጋፍ

እንደሚያደርግናየተለያዩ ፓኬጆችን በማዘጋጀት የመደገፍ አዝማሚያ አሳይቶ ነበር፡፡ ግን ብዙም አልገፋበትም፡፡ በሂደት ድርጀቶች የሚያቀርቡት ማህበራዊ ግልጋሎትና የሥራ ፈጠራ እገዛ ለመንግስት የቅቡልነት ጥያቄ ሊፈጥር እንደሚችል መረዳት ጀምረ፡፡ ከልማቱ ባለፈ በተለይ ለታዳጊ ሀገራት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ፈሰስ በማድረግ የማይናቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ የመንግስትን የልማት ክፍተት በመሸፈን የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማስፋት ፣በመረጃ እና በተለያዩ የሲቨል ስራዎች በበጎ ፍቃደኝነት በሰፊው ተንቀሳዋል፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ በ1997 ምርጫ ድርጅቶች በህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በታዛቢነትና በምርጫ አስፈጻሚነት በመሳትፍ ለምርጫው መሳካት ከፍተኛ አስተዋዖ አበርክተዎል፡፡

ህብረተሰቡ በምርጫው እንዲሳተፍ መቀስቀስ፣የምርጫ ህጉን በማስተመማር፣ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ሒደቱን በመታዘብ እና የተለያዩ ውይይቶችን በማከናወን ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በጊዜውም እኔ በምሰራበት ድርጅት አለም አቀፍ የጸረ-ድህነት ጥሪ (Global Call Against Poverty – GCAP) በሚል ርዕስ በተካሄደ በAction Aid Ethiopia እና Organization for Social Justice Ethiopia (OSJE) በጋራ በተሰጠ የገንዘብ ድጋፍ ተካሂዶ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ህብረተሰቡ ለድህነት ቅነሳ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የቅስቀሳ ኘሮግራም እናካሂድ ነበር፡፡

GCAP ትልቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ነበር የሚገርመው ነገር ከሀገሪቱ ምርጫ ጋር በመገናኝቱ መጨረሻው አላማረም፡፡ ፕሮጀክቶቹ በሙሉ ያለቅድመ ሁኔታ በመንግስት ተከለከሉ፡፡ ቀጥሎም አስተባባሪዎች አቶ ዳንኤል እና አቶ ነፃነት በግፍ ካለምንም ጥፋታቸው ለእስር በቁ፡፡ በዚህም ስራ የተሳተፉ ሌሎች ድርጅቶች ጭራሽኑ ተዘጉ፡፡ ቀሪዎቹም ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡

ምርጫ 1997 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በምርጫ ታዛቢነት እንዳይካፈሉ ምርጫ ቦርድ ከለከለ፡፡ በቅስቀሳው ብቻ እንድንሳተፍ ተወሰነ፡፡ ሆኖም አስራ ሁለት የሚደርሱ በምርጫው የገንዘብ ድጋፍ አግኝተው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ድርጅቶች Action Aid Ethiopia, Organization for Social Justice Ethiopia (OSJE), Initiative Africa, CRDA, Youth Network for Sustainable Development, Afro-flag Ethiopia ምርጫ ቦርድን ከሰሱ፡፡ በፍርድ ቤትም ትዕዛዝ ምርጫውን መታዘብ እንደሚችሉ ህገ-መንግስቱም ሆነ የመተዳደሪያ ደንባቸው ይፈቅዳል ብሎ ወሰነ፡፡ በዚህም በ1997 ዓ.ም በሀገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ያለበት ምርጫ ተደረገ፡፡ የምርጫው ሂደትም ቀደም ሲል ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ነፃና ግልጽ ነበር፡፡ ሆኖም በወቅቱ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አንዱ የነበረው ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ በሀገሪቱ ደረጃ በቅድመ ቆጠራው እንዳሸነፈ ተነገረ፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ገዥው ፓርቲ ከበረሃ ተዋግቼ የያዝኩትን ስልጣን በምንም ዓይነት አለቅም አለ፡፡ በአገሪቱ ውጥረት ሰፈነ፡፡ የተቃዎሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው አሸንፊያለው ስልጣን ይገባኛል አሉ፡፡ መንግስት ስልጣኑን ለማስረከብ ፍቃደኛ ባለመሆኑ የምርጫውን ውጤት ቀልብሶ ወታደራዊ ዕዝ በማቋቋም መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ አደረገ፡፡ ለሽንፈቱ መንስኤ የሆኑትን አንድ ባንድ አሰራቸው፡፡ በዋነኛነትም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህብረተሰቡን ስለ መብቱ ያስተማሩ፣ በምርጫው ግንዛቤ ያስጨበጡ እንዲሁም በምርጫው ታዛቢ የሆኑ በመሆናቸው የጥቃቱ ዋና ዒላማ ሆኑ፡፡ ስለሆነም ፓርቲው የተለያዩ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በስም ለይቶ የገንዘብ ድጋፍ የሰጡ፣ ምርጫ ቦርድን የከሰሱ ፣በምርጫ ቅስቀሰሳ የተሳተፉ በማለት ተገደሉ፣ ለእስርና ስደት በቁ፡፡

የወያኔ መንግስትም በዋነኛነት ጠላቴ ያላቸውን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በምርጫ እንዳይሳተፉ፣ ህብረተሰቡን ግንዛቤ በሚያስጨብጥ የመብት ጉዳይ እንዳይሰሩ እና በሌሎች ጉዳዮች ህግ አወጣ፡፡ በህጉም ብዙ ድርጅቶችን ከእንቅስቃሴ አገደ፡፡ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግስታት ህጉን አፋኝ እንደሆነ ማሳሰቢያ ቢሰጡም ሰሚ አላገኙም፡፡ በሀገር ውስጥ ያሉ መያድ ድርጅቶች ባስነሱት ተቃውሞ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ በጽ/ቤታቸው ስብሰባ ጠሩ፡፡ ሆኖም ከስድባና መስፈራሪያ ውጭይሄ ነው የተባለ በቂ ምክኒያት ሳይሰጥ ተበተነ፡፡

የወያኔ መንግስት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የሚሰልሉለት ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የፈጠረ ሲሆን ከእነዚህም በዋነኛነት Consortium for population, Health & Environment (PHE-Ethiopia) and Ethiopia Civil Society Forum ይገኙበታል፡፡ የወያኔ መንግስት ሰላዮች ናቸው፡፡ በቅርበት አውቃቸዋለው፡፡ ለእነሱ የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህግ አይሰራም፡፡ በተለይ 70/30 የሚባለው አይመለከታቸውም በጉልበትም ድርጅቶች የነሱ አባል እንዲሆኑ ያደርጋሉ፡፡

ከብዙ ማስረጃዎች አንዱን ላቅርብ በህጉ መሰረት ኔትወርኮች/ኮንሰርትየም ገንዘብ ለአባላቶቻቸው ያስተላልፋሉ እንጂ መሬት ላይ የሚታይ ስራ መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡ ህጉን ተላልፈው በተግባር ቢገኙ ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፕሮጀክቶቻቸው ይሰረዛሉ፡፡ ለእነ Consortium for population, Health & Environment (PHE-Ethiopia) and Ethiopia Civil Society Forum ይፈቀዳል፡፡

ሌላው እነዚህ ድርጅቶች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኤጀንሲ ብሎ ባቋቋመው ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ ሌሎች ድርጅት 70/30 አልጠበቃችሁም፣ እንቅስቃሴያችሁ በመጠኑም የመብት ጉዳይ ላይ ሰርታችኋል ተብለው ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው እንኝህ ግን ከኤጀንሲው ጋር በመሆን ምክንያት በመስጠት እንዲዘጉ ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

ሀገር ውስጥ ካሉ የሚዲያ ተቋማት ጋር ባለኝ ግንኙነት በምሳሌነት ለመጥቀስ የአሁኑ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ከእነዚህ እና ከወያኔ አጋር ድርጅቶች በስተቀር ለማንኛውም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሚድያ ድጋፍ እንዳይደረግ ወይም የዜና ሽፋን እንዳይሰጥ ተብሎ በዟሪ ደብዳቤ ታዟል፡፡ በተቃራኒው በመንግሰት ለሚደገፉ ድርጅቶች ከፍተኛ የዜና ድጋፍ ይሰጣል፡፡ የሰሩትን ስራ ተጋኖ ይቀርባል፡፡ ጠሩት ስብሰባ የመንግስት ባለስልጣና የመገኝት ግዴታ አለበት፡፡ በአጠቃላይ እኛ በሀገር ውስጥ ያሉ መያድ ወካዮች ናቸው በማለት የወያኔ መንግስት ሹመት ሰጥቶዋቸዋል፡፡

የሚገርመው ለእነዚህ ድርቶች አባል ያልሆነ ፍቃድ ለማደስ በሚኬድበት ጊዜ ብዙ መከራ ይደርስበታል፡፡ ባለመተባበር ፍቃድህ ሊነጠቅ ይችላል፡፡ ከሁለቱ ድርጅቶች ጋር አብረህ የምትሰራ ከሆንክ ከተሰጠህ ዓላማ ውጭ የፖለቲካ ስራ እንድትሰራ ትደረጋለህ፡፡ ባንተ ድርጅት ስም የፈለጉትን ፌርማዎች ይፈራረማሉ፡፡
ይቀጥላል…

LEAVE A REPLY