ባለ ሰልስቱም ባለ ቀብሩም መላኩ /ታሪኩ ደሳለኝ/

ባለ ሰልስቱም ባለ ቀብሩም መላኩ /ታሪኩ ደሳለኝ/

ከቀን ወደ ቀን የሞቿች ወገኖቻችን ቁጥር እያሻቀበ ነው። 40 ብለን ከድንጋጢያችን ሳንወጣ 80 መድረሱን እንሰማለን ሰማኒያን ሳናምን 100 መሻገሩን እንረዳልን። በየቀኑ ቁጥሩ እየጨመረ ዛሬ የሟቿች ብዛት አንድ መቶ አስራ አምስትን ተሻግሯ።

መላኩ 12ኛ አመቱን ያዞል የ6ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ ነው። በስለት የተወለደ ነው ይላሉ ጎረቤቶቹ ለዚህ ነው እናቱ “መላኩ” ብላ ስም ያወጣችለት። ቅዳሜ ምሽት የቆሻሻው ክምር ከመናዱ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በፊት መላኩ ቤቱ በር ላይ እግሩን እየታጠበ ነው በግዜ ሊተኛ። በመሃል ስሙ ተጠራ “መላኩዬ” ተባለ አልዞረም እንደ ሁል ጊዜው ደስ አለው። እናቱ ብቻ ነች እንደዚህ ብላ የመትጠራው።

ከቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ከገዳም ግዳም ዞራ ለመና ፆሎቶ ተሰምቶ በስተርጅና ያገኝቸው ልጇ ነው። ከላይም ከታችም እሱ ብቻ ነው ልጇ “መላኩ”። መላኩ ጆኩ ውስጥ የቀረችውን ውሃ እግሩ ላይ አፍሶ ከተቀመጠበት ተነሳ። እናቱ ከግሩ እስከ ፀጉሩ በስስት እየተመለከተችው “አንገት ልብስህን አጥቤልሀለሁ በጠዋት ቤተክርስቲያን ትሄዳል” አለቸው። እናት ስለቷን አጓድላ አታውቅም አበባ እማማ ብሎ መጥረት ከጀመረበት ግዜ ጀምሮ እድጅክን አሳልመዋለሁ ብላላች ለአምላኳ ይህው ስንት አመቷ ቃሏን እንዳከበረች። ለዛ ነው ነገም ይዛው የምትሄደው። “ነገ ትሄዳላችሁ ወይ ብለህ እትዬ ፅጌን ጠይቅ ጠዋት እንድንቀሰቅሳቸው” አለችው “እሺ” አለ መላኩ ጆኩን ሊሰጣት እጁን ዘረጋ እናት እጁን ይዛ ወደራሷ ጉተተችው እየሳቀ ልጅ ተጉተተ ግንባሩን ጉንጩን ሳመችው ፀጉሩን ደባበሰችው። እቺ እናት ለመጨረሻ ግዜ ልጇን እንደሳመች ለመጨረሻ ግዜ የልጇን ፀጉር እንደዳበሰች አላወቀችም።

መላኩ ከእቅፏ ወጥቱ ወደ ጉረቤቶቹ ቤት መሄድ ጀመር አረማመዱ የተንቀራፋባት እናት ልጇን እየተመለከተች “ቶሎ ቶሎ ብል እዚሁ ቆሜ እጠብቅሃለሁ” አለቸው መላኩ የናቱን ትዛዝ ተገበራ ብትናንሽ እግሮቹ እየሮጠ ሄድ። አሁንም ይቺ እናት ልጇን ከሞት እያተረፈችው መሆኑን ከቶም አልተረዳችም። በዛች የሰክንድ ግማሽ አይን ተገልጡ ከሚከደንበት ፍጥነት በባስ ሁኔታ የቆሻሻው ተራራ የላዩ ወደታች የታቹወደ ላይ ሲደረመስ መላኩ ወደ መንገዱ ዳራ ደርሷል። እድጅ የቆመችው የልጆን ጀርባ በርቀት እያየች መመለሱን የምትናፍቀው የመላኩ እናት ከቤት ሆኖ ልጁና ሚስቱን የሚጠብቀው አባዎራ ላይ የቆሻሻው ተራራ ተናደባቸው።

ይህ በሆነ በሁለተኛው ቀን የመላኩ አባት ሲቀበር መላኩ እራሱን በግማሽ አላወቀም በጉረቤቶቹ ክንድ ተይዞ እንባው ብቻ ይፈሳል። ዛሬ ከአራት ቀን በኃላ የመላኩ እናት አስክሬን ከቆሻሻው ስር ወጥቶል። ለመላኩ ዛሬ የአባቱ ስልስት ሲሆን የእናቱ ደግሞ ቀብር ነው። መላኩ ይህንን እንኮን በቅጡ አልተረዳውም። ልጅ መላኩ ሆይ እግዛብሔር ብርታቱን ይስጥህ።
እንግዲህ የመላኩና የመስሎቹ እጣ ምን ይሆን? የማን ሀለፊነትስ ነው? የኛስ ግዴታ ምንድን ነው?

መጋቢት 7/09ዓ.ም
ቆሼ ሠፈር

LEAVE A REPLY