ኢትዮጵያዊው የምግብ ቤት ባለቤት በሰው እጅ ተገደለ

ኢትዮጵያዊው የምግብ ቤት ባለቤት በሰው እጅ ተገደለ

ዜና ኢትዮጵያ ነገ፦ ኢትዮጵያዊው የምግብ ቤት ባለቤበናሽቪል ቴነሲ የሚገኘው አይቤክስ የኢትዮጵያውያን ምግብ ቤት ባለቤት የሆነው ግጥም ደምሴ እስካሁን ባልታወቀ ሰው መገደሉ ተገለጸ።

ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ የተለያዩ የአካባቢውና አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃ እንደዘገቡት፣ ግጥም ወደ እኩለ ሌሊት አካባቢ አይቤክስ በመባል የሚታወቀውን ምግብ ቤቱን ዘግቶ በመውጣት ላይ እያለ አንድ ማንነቱን ለመደበቅ የተሸፋፈነ ሰው ድንገት በጥይት መትቶ እንደገደለው ለማወቅ ትውችሏል።

የ41 አመቱ ጎልማሳ ግጥም ቀድሞ የአይቤክስ ማርት ባለቤት የነበረ ሲሆን የምግብ ቤት ሥራ የጀመረው በ2015 ዓ.ም ነው።

ስለገዳዩ ማንነት እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ሁኔታው ዝርፊያ ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ ግን ጥቆማዎች አስረድተዋል፡፡ በቂም በቀል የተደረገ አሰቃቂ ግድያ መሆኑን የሚጠቁሙት መረጃዎች እያስረዱ ባሉበት በአሁኑ ሰአት እስካሁን የገዳይን ዱካ የሚያመላክቱ ጥቆማዎችን የአካባቢው ፖሊስ በማፈላለግ ላይ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ይህ አሳዛኝ ክስተት በናሽቪል ቴነሲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እጅግ አስደንግጧል። ፖሊስ ገዳዩን ለማግኘት ለሚያደረገው ጥረት የሚጠቅም መረጃ ለማሰባሰብ የስልክ ቁጥር ያሰራጨ ሲሆን ማናቸውም ጥቆማ ለክትትሉ ስለሚረዳ ጥቆማ ካላችሁ በ 615-742-7463 ደውሉ ሲል ይፋ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም ፖሊስ የቴክስት መለክት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ ጠቋሚዎች መስመር ያዘጋጀ ሲሆን “CASH” የሚል መልእክት እንዲተው 274637 የሚል ቁጥር አስቀምጧል፡፡

በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱን ላጣው ግጥም ደምሴ ቤተሰቦችና መላ ኢትዮጵያዊያን አምላክ መጽናናትን ይስጥ፡፡
ኢትዮጵያ ነገ ዝግጅት ክፍል /ኢነዝክ/

LEAVE A REPLY