‎አቶ ሃብታሙ አያሌው በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የሚደረግውን አስከፊነት ስቃይ በይፋ ተናገረ

‎አቶ ሃብታሙ አያሌው በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የሚደረግውን አስከፊነት ስቃይ በይፋ ተናገረ

/Ethiopia Nege News/፦ የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ፓለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው ማእከላዊን ጨምሮ በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ እስር ቤቶች የሚፈጸሙ አሰቃቂ የማሰቃየት ድርጊቶችን በይፋ ተናገረ፡፡

ለሁለት አመታት በእስር ላይ በነበረበት ወቅት አናቱ ላይ እጅግ ቀዝቅዝዛ ነገር ያስቀምጡና በኩርኩም ይመታ እንደነበርና ከዛ ምን አንደተደረገ እንኳን ማወቅ እስክሚሳነው ያሰቃዩት እንደነበር የገለጸው ሃብታሙ አያሌው ይህ በብዙ እስረኞች ዘንድ የተለመደ ድርጊት መሆኑን በመግለጽ አስከፊ በሆነ መልኩ እጆቻቸው ማስቀያ ብረት ላይ ተሰቅሎ ብልታቸው ላይ ውሃ የሚንጠላጠልባቸው እስረኞች ህይወታቸውን እስከማጣት የደረሱበት ዘግናኝ ተግባራት በመጥፎነቱ በሚታወቀው የአዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት እንደሚፈጸም ተናግሯል፡፡

አቶ ሃብታሙ በህክምና ከሚገኝበት አሜሪካን ሃገር ለቪኦኤ ራዲዮ ቃለ ምልልስ የሰጠ ሲሆን የፊጥኝ የታሰረ ሰው ከብዙ ስቃይ በኋላ ከማን ጋር ግንኙነት አለህ ይባልና በሚፈልጉት መልኩ በጻፉት ወረቀት ላይ እንዲፈርም ይደረጋል ሲል በሲቃ ድምጽ ሲናገር ተስተውሏል፡፡

በኢትዮጵያ መታሰር የንቁ ዜግነት መታወቂያ ሆኗል የሚለው ሃብታሙ አያሌው ይህች እነሱ የሚገዟት ሃገር ነጻ ሆና እንድትኖር ከየ አቅጣጫው ዋጋ የከፈሉ አባቶች ልጆች መሆናችን ሊያሸልመን ሲገባን የእነሱ ልጆች እየተባልን መሰቃየታችን ያሳዝናል ሲል ስሜቱን ገልጿል፡፡

የመጀመሪያ ክፍል

ክፍል ሁለት

/

      ቃለ ምልልሱን ለማዳመጥ ይህንን ይጫኑ
/

/Ethiopia Nege March 24, 2016/

LEAVE A REPLY