በሀገራችን ሕግ አህያን ማረድ ወንጀል ነው! ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ! /ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን...

በሀገራችን ሕግ አህያን ማረድ ወንጀል ነው! ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ! /ሠዓሊ አምሳሉ ገብረኪዳን አርጋው/

ትናንትና በመጽሐፈ ገጽ መዝገቤ (በፌስ ቡክ አካውንቴ) ይህችን አረፍተነገር ጻፍኩ፦

“አየ እናንተ!!! የአህያ ቄራ በመከፈቱ ተደነቃቹህ? ወያኔ እኮ የሆነ ቦታ የሰው ሥጋ የሚበሉ ማኅበረሰቦች
ቢኖሩ የሰው ቄራ ከፍቶ የሰው ሥጋ ለእነሱ እስከማቅረብ ድረስ የሚሔድ አረመኔና ኢሞራላዊ (ኢቅስማዊ) ፣
ኢግብረገባዊ፣ ኢሃይማኖታዊና ኢባሕላዊ የወንበዴ ቡድን እኮ ነው! እስከ አሁን አታውቁም እንዴ? ስትገርሙ!
ለገበያ አልቀረበም እንጂ ወያኔ እኮ ስንትና ስንት የሰው ቄራዎች አሉት!!!” ብየ፡፡ ታዲያ አንዱ ከዚህ በታች
ያለውን አስተያየት ጻፈ፡፡

“አምሳሉ የአህያ ቄራ መከፈቱ እንዴት እንዲህ እንዳማረራቹ
አልገባኝም። እናንተ ብሉ አልተባላችሁ፤ እረዱ አልተባላችሁ፤
እዩም አልተባላችሁ…. ታድያ ምን ያገባችኋል? በሬና በግ
ታነክታላችሁ፤ ሱማሌ ክልል ደሞ ግመል ይበላሉ፤ ኩባ፣
ቬትናምና ቻይና ደግሞ አህያ ይበላሉ። ምን ችግር አለው?
አህያ ሸኾናው ድፍን ስለሆነ አይበላም የሚል ከሙሴ ጋር
የተቀበረ ምክንያት አትስጠኝ። በሬ ከበላህ አህያ በምንም ነውር
አይሆንም። ሳይንሳዊ ምክንያት የላቹም። አገሪቱ ደግሞ
በሃይማኖት ሕግ አትተደርም። ቆሻሻ የሚበላ ሕዝብ ይዘን አህያ
ለምን ይሸጣል ስትሉ አታፍሩም። እሱን በልተን ከረሃብ በወጣን
በማን እድል። ወያኔ ትምክተኛ የሚላችሁ እናንተን መሆን
አለበት። ወያኔን ብጠላም ለናንተ ግን መድሃኒት ነው።” ብሎ ጻፈ፡፡ እኔም የሚከተለውን መለስኩለት፦

“”@…. እንዳልከው ነው! ለሞራል (ለቅስም) ያለህ ዋጋና ግምት ምንም ወይም ባዶ ከሆነ ከዚህ የተለየ
ሊሰማህ የሚችል ነገር አለመኖሩ የሚጠበቅ ነው፡፡ ለሞራል (ለቅስም) ክብርና ዋጋ ላለው ለሚሰጥ ለአንድ ዜጋ ግን
የሀገሩ ባሕል የሚጸየፈውና “ነውር!” የሚለው ነገር በገዛ ሀገሩ በይፋ ሲፈጸም ሲያይ በቀጥታ ከሥነ ልቡና እስከ
የሕሊና ሰላምና ምቾት በማጣት በመታወክ፣ ምግብ በሆዱ ውስጥ እንዳይረጋጋ በማድረግ ወይም በማስታወክ በመሳሰሉት
ችግሮች ይጠቃል፡፡ ለዚህም ነው የሀገሪቱ ሕግ “ሕዝቡ ተቀብሎት ከሚኖረው ባሕልና አስተሳሰብ ውጪ የሆነና
የሚቃረን ተግባርን መፈጸም ወንጀል ነው!” ሲል የሚደነግገው፡፡

ወገኔ ቆሻሻ ላይ የወደቀ ምግብን እየተመገበ ያለውና በረሀብ አለንጋ እየተገረፈ ያለው ሀገሩን በመነጠቁ፣ በገዛ
ሀገሩ ሠርቶ የመብላት፣ መጠለያ የማግኘት መብቱን በመነጠቁ፣ በመገለሉና የበይ ተመልካች በመደረጉ እንጅ የሚበላ
በመታጣቱ፣ ዝናብ በመጥፋቱ አይደለም፡፡ ሀገራችን ካላት የውኃ ሀብት የተነሣ “የአፍሪካ የውኃ ማማ!” መባሏን
አታውቅም? ችግራችን አንተ ያልከው አለመሆኑንማ ምግብ ከቆሻሻ ጋር ከመደፋቱ እኮ ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡

ካፌ ውስጥ ተቀምጠህ ወይም በአንድ ሌላ ሕዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ ላይ ባለህበት ሁለት ዋልጌዎች ተነሥተው በግልጽ
ወሲብ ሲፈጽሙ ብታይ ለሞራል (ለቅስም) ዋጋ ለማትሰጠው ላንተ ምንም ላይመስልህ ይችላል፡፡ እንዲያውም
ትዝናናበትም ይሆናል፡፡ ሞራል (ቅስም) ላላቸው ሰዎች ግን ይህ ተግባር ፈጽሞ ሊታገሱት የማይገባና የሚቀፍ፣
በመመልከታቸው ብቻ ለአካላዊና ሥነ ልቡናዊ ሕመም ሊዳረጉ የሚችሉበት አስቀያሚ፣ አስጸያፊ፣ ቀፋፊ ተግባር ነው፡፡
ባጭሩ ለሰው ልጅ (ልብ በል ለሰው ልጅ ነው ያልኩት ለአራዊት አይደለም ያልኩት) ትልቁ ሀብቱና ንብረቱ
የሁለንተናዊ ጤናውና የደኅንነቱ ዋስትና በሞራል (በቅስም) ሕጎች የሚጠብቀው የሕሊና ወይም የውስጥ ሰላሙ ነው፡፡
ይሄ ከሌለህ ታብዳለህ! ጤነኛ ወይም የተረጋጋ ሥነልቡና ያለህ ልትሆን አትችልም! ከአካልህ በስተቀርም ሰው
የሚያሰኝ የሰው ልጅ መለያ ባሕርያት አይኖሩህም፡፡

የሙሴ ሕግ ከሙሴ ጋር አልተቀበረም! የሀገራችን ሕዝብ ባሕሉ አድርጎት እየኖረበት እየተዳደረበት የነበረና አሁንም
ያለ መሆኑን የማታውቅ ከሆነ ፈጽሞ አታውቀንምና እኛን በተመለከተ ምንም ነገር አትናገር እሽ? ወገናችን እንኳንና
እርም የሆኑ እንስሳትን ለምግብነት ሊጠቀም ቀርቶ እልቂት ባደረሰብን ረሀብ ውስጥ ሆኖ እንደቅጠል እየረገፈ
ባለበት ሰዓት እንኳ ከብቶቹን ለመመገብ የሚቀፈው የማይጨክን ከፍተኛ የሞራል (የቅስም) እና የሰብአዊነት ደረጃ
ላይ ያለ ክቡር ሕዝብ ነው፡፡ “” በማለት፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

amsalugkidan@gmail.com

LEAVE A REPLY