የክቡር አርበኛ ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አስከሬን ግባተ መሬት ዛሬ ተፈጸመ

የክቡር አርበኛ ሌ/ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አስከሬን ግባተ መሬት ዛሬ ተፈጸመ

/Ethiopia Nege News/፦ የታላቁ አርበኛ የሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ እሁድ ሚያዚያ 1 ቀን 2009 ዓ.ም አርበኞችና ታዋቂ ሰዎች በሚቀበሩበት በቅድስተ ስላሴ ካቴድራል በክብር ተፈጸመ፡፡

አባት አርበኞች፡ ቤተሰቦቻቸውና በርካታ ህዝብ የተገኘበት የቀብር ስነ ስርዓት ወጣት ኢትዮጵያዊያንና አባት አርነኞች በቀረርቶና ሽለላ በማጀብ ታላቁን አርበኛ ሽኝት አድርገውላቸዋል፡፡

ከ15 አመታቸው ጀምረው የጠላት ሃይል ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመጣል የሚታወቁት ሌ/ጄኔራል ጃገማ ኬሎ በኢጣሊያ ወረራ ወቅት በአርበኝነት ጀብድ በመፈጸም ከበርካታ አገር አቀፍና አለም አቀፍ እውቅና ያገኙ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ጎን ተሰልፈው ሃገርን ከወራሪ ለመከላከል ያደረጉት ተጋድሎን ያካተተው የህይወት ታሪካቸው ተነቧል፡፡

ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ የህይወት ታሪካቸው በመጽሃፍት ከመታተሙም በላይ በራሳቸው ድምጽ ያሳለፉትን ውጣ ውረድ የተረኩባቸው ቃእምልልሶች ለታሪክ መመዝገባቸው ይታወቃል፡፡

/Ethiopia Nege April 9, 2017/

LEAVE A REPLY