በግብጽ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች በፈነዳ ቦምብ 37 ሲሞቱ ከ70 በላይ ቆሰሉ

በግብጽ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች በፈነዳ ቦምብ 37 ሲሞቱ ከ70 በላይ ቆሰሉ

/Ethiopia Nege News/፦ በግብጽ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖች በፈነዳ ቦምብ 37 ሲሞቱ ከ70 በላይ ቆሰሉ

የሆሳዕና በአል ለማክበር በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል በተሰባሰቡ ክርስቲያኖች ላይ በተሰነዘረ የቦንብ ጥቃት 37 መሞታቸውንና ከ 70 በላይ ምእመናን መቁሰላቸው ተዘገበ፡፡

የመጀመሪያው ጥቃት ታንታ በሚባለው ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ሲሆን 25 ሰዎች መስዋእት እንደሆኑና በሁለተኛው የቦምብ ጥቃት 11 ክርስቲያኖች አሌክሳንደሪያ በሚገኘው ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን መሰዋእትነት መክፈላቸው ታውቋል፡፡

አንዱ ጥቃት የተፈጸመበት የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፅህፈት ቤትና የፓትሪያርኩ የብፁዕ አቡነ ቴዎድሮስ 2ኛ መንበር መገኛ ነው፡፡

ሶስት ፖሊሶች አደጋውን ለማስቆም ባደረጉት ጥረት መሞታቸውን የግብጽ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ከገለጹት ውጭ በጥቃቱ የተሰው ሰዎች ዝርዝርም ሆነ ብጹዓን አባቶች የጥቃቱ ሰላባ ስለመሆናቸው ይህ ዘገባ እስኪጠናቀር አልተገለጸም፡፡

ለጥቃቱ የእስልምና መንግስትን ለማቋቋም የሚንቀስቀሰው አይሲስ በመባል የሚታወቀው አክራሪ ቡድን ሃላፊነቱን ወስዷል፡፡

የግብፁ መሪ አብዱል ፋታህ አልሲሲ ድርጊቱ የአሸባሪዎች ጥቃት ነው ሲሉ አውግዘው የአስቸኳይ የሃዘን ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ተዘግቧል።

/Ethiopia Nege April 9, 2017/

LEAVE A REPLY