“ኢትዮጵያ” የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ነጠላ ዜማ ቅዳሜ – (15 አፕሪል) ይለቀቃል

“ኢትዮጵያ” የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ነጠላ ዜማ ቅዳሜ – (15 አፕሪል) ይለቀቃል

(ምስል - ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ እና ማናጀሩ ጌታቸው 
ማንጉዳይ የማስተሩን ውል ከፈጸሙት ባለሃብቶች ጋር)

“ኢትዮጵያ” የተሰኘው የቴዲ አፍሮ አዲሱ ነጠላ ዜማ በመጭው ቅዳሜ ሚያዝያ 8 ቀን (15 አፕሪል) ለህዝብ ይለቀቃል። ነጠላ ዜማው በእለተ ትንሳኤ ሲለቀቅ ሙሉውን ስራ የያዘው አልበም ደግሞ በዳግም ትንሳኤ በመላው አለም ለገበያ ይቀርባል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቴዲ አፍሮ አልበም በአዲስ አበባ ኤፍ. ኤም ራዲዮ ጣብያዎች እንደሚነገረው የተጋነነ አነጋጋሪ ጉዳይ አልፈጠረም። የመዘግየቱ ምክንያትም አልበሙ ጥራት እንዲኖረው፣ በስራዎቹ ላይ በርካታ ማሻሻያ እየተደረገባቸው መሆኑን በድምጻዊው የህዝብ ግንኙነት በኩል ተነግርሯል። አንቱ የሚባሉ የሚዚቃ አቀናባሪዎች አጫራቸውን ያሰረፉበት ይህ “ኢትዮጵያ” የተሰኘ አልበም “ድንቅ” የሚሰኝን የጥበብ ውጤት እንደሆነ ከወዲሁ ተነግሯል።

የአልበሙ ማስተር አንዴ በ50 ሚሊዮን ብር፣ ሌላ ግዜ በ15 ሚሊዮን ብር ፣ አሁን ደግሞ በ5 ሚሊዮን ብር ተሸጠ እየተባለ በኤፍ. ኤም ራዲዮ ጣብያዎች ጭምር የሚወራውም መላ ምት መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

ሕዝብ በጉጉት እየጠበቀ ያለው ይህ አልበም እስከ አንድ ሚሊዮን ኮፒ ሊሸጥ እንደሚችል ይገመታል። ይህ ደግሞ እስካሁን በኢትዮጵያ ከታተሙ የሙዚቃ ስራዎች ሁሉ የመጀመርያው ያደርገዋል። ማስተሩን ባለሃብቶች የገዙት ሲሆን የህትመት ስራው በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር እየተከናወነ ይገኛል።

አዲሱ አልበም ተሰራጭቶ እንዳበቃ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከአቡጊዳ ባንድ ጋር በመሆን በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ ከተሞች እየተዘዋወረ ስራውን ያሳያል።

/የ EMF ዘገባ ነው/

LEAVE A REPLY