ከተከዜ ወዲህ /መስፍን ማሞ ተሰማ/

ከተከዜ ወዲህ /መስፍን ማሞ ተሰማ/

ከተከዜ ወዲህ ፤ አህያ አለቀሰ

ባያቶቹ ጀርባ ፤ ባባቶቹ ጉልበት

በልጆቹ ስቃይ ፤ ባቆማት ኢትዮጵያ

ባቀናት ቀዬ ላይ . . .

ደደቢትን አልፎ ተከዜን ሲሻገር

የምዕተ ዓመታት ውለታው ተረግጦ

“ደሳለኝ” ተንቆ ፤ “ደሳለኝ” ተካደ።

በገዛ ሀገሩ

በገዛ መንደሩ

ለባዕድ ተሸጠ።

በገዛ መሬቱ

ባያት ቅም አያቱ

በባዕድ ጉሮኖ

በባዕድ ታግቶ . . .

በኢህአዴግ ቡራኬ ፤ በቻይናዎች ካራ

ለወያኔ ንዋይ ፤ አንገቱን ቢቀላ

ለዶላር ቢሰዋ . . .

ከ ተ ከ ዜ ወ ዲ ህ ዋ ! አለ አህያ !!

***************************************************

ሚያዚያ 2009 ዓ/ም (አፕሪል 2017)-ሲድኒ አውስትራሊያ

LEAVE A REPLY