ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ

ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ ፍ/ቤት ቀረቡ

11 ገጽ ያለው የክስ መቃወሚያም ማቅረባቸው ታውቋል።

የክስ መቃወሚያው የቀረበው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን

በቀረበው የክስ መቃወሚያ ያተኮረው በዋናነት “ ክሴ ከእነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ እና ጃዋር መሀመድ ጋር አብሮ ሊታይ አይገባም፤ የእኔ የህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ሊቀ መንበር ነኝ፤ ከእነሱ አላማና አፈጻጸም ጋር ፍፁም የማይገናኝና ላለፉት 20 አመታት የሀገሪቱን ህገ_መንግስት መሰረት አድርጌ ለሀገር በጎ አስተዋፅዖ በማድረጌ ክሴ ተነጥሎ ሊታይ ይገባል።“ ይላል።

“ቤልጂየም ብራስልስ ለህዝባዊ ስራ ነው የሄድኩት፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቁጥር 11/2009 ዓ.ም መሰረት ኮማንድ ፖስቱ ያወጣው የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያ አንቀጽ 2/1 ስር የተመለከተውን ተላልፏል የተባለውን እቃወማለሁ“ ሲሉ በመቃወሚያቸው ተጠቅሷል።

“በ2008 እና 2009 ዓ.ም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ለተከሰተው ሁከት እና አለመረጋጋት እኔ ልጠየቅ አይገባም“ ሲሉም ተቃውሞዋቸውን ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል።

መቃወሚያውን የሰማው ፍ/ ቤትም መቃወሚያው ላይ የአቃቤ ህግን አስተያየት ለመስማት ለሚያዚያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ የዶክተር መረራ ፓርቲ የሆነው

“የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ” በህዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት የማባባስ ሚና ተጫውቷል በሚል ምክኒያት ክስ እንደሚመሰረትበት ታውቋል።

LEAVE A REPLY