በተ.መ.ድ የሰብዓዊ መብቶች ዋና ዳሬክተር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እቅድ ይዘዋል ተባለ!

በተ.መ.ድ የሰብዓዊ መብቶች ዋና ዳሬክተር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት እቅድ ይዘዋል ተባለ!

ግብዣው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ተብሏል

/Ethiopia Nege News/ :- በሰብዓዊ መብት አያያዝ የማይሆንላት ኢትዮጵያ፤ በተለይ ደግሞ አንድ ዓመት ከመንፈቅ በላይ  ያስቆጠረው “ህዝባዊ ተቃውሞ” ከተከሰተ ወዲህ የተለያዩ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የሀገሪቱን “የሰብዓዊ መብት” አያያዝ የሚኮንን መግለጫ በተደጋጋሚ ሲያወጡ መቆየታቸው ይታወቃል።

  የተባበሩት መንግስታት የብሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም (United Nations High Commissioner for Human Rights-UNHCHR) ህዝባዊ አመፁን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በንፁኃን ዜጎች ላይ እየወሰደ ስላለው ግድያንና የገፍ እስራት ሲቃወም ቆይቷል።

     ኮሚሽንኑም በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈፀመውንና እየተፈፀ ያለውን የመብት ጥሰት በገልተኛ አካል እንዲጣራ የጠየቀ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት “ከሉዓላዊነት” ጋር በማያያዝ ጥያቄውን አለመቀበሉን  የሚታወስ ሲሆን  ዛሬ ደግሞ  በኢትዮጵያ መንግስት ጋባዥነት የተ.መ.ድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት  ዛይድ ረዓድ አል-ሁሴን  የመንግስትን ግብዣ በመቀበል እ.ኤ.አ አቆጣጠር  ከግንቦት 2 እስከ 4/5/17 የሚቆይ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ታውቋል።

  ዛይድ ረዓድ በቆይታቸው ወቅትም ከጠ/ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ፣ ከአፈ_ጉባዔ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት “ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ስላለው የሰብዓዊ መብቶች  ሁኔታ” ትኩረት ሰጥው እንደሚወያዩ ተገልጿል።

   ኮሚሽነሩ በተጨማሪ  የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን  ኮሚሽነር ከሆኑት ከአቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሔር፤ ከሲቪል ማህበረሰብ  ድርጅቶችና ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋርም እንደሚገናኙ መረጃው ያመለክታል።

    ኮሚሽነር ዛይድ ረዓድ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊ/መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት እና ከሌሎች ከህብረቱ ባለስልጣናት ጋር  “ተ.መ.ድ እና የአፍሪካ ህብረት”  የተሻለና የተቀናጀ  “የሰብዓዊ መብት” አሰራር ስለሚፈጠርበት ሁኔታ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ከአለማች ሀገራት ከመጨረሻዎቹ ታርታ የምትመደብ  መሆኗ የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY