በጅማ ከተማ አዳራሽ ተደርምሶ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

በጅማ ከተማ አዳራሽ ተደርምሶ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ

/Ethiopia Nege News/:- በጅማ ከተማ መንቲና ቀበሌ ማሪያም ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የቀበሌ አስተዳድር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ተደርምሶ፤ አዳራሹ ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ አቅመ-ደካማ(አዛውንቶች) ውስጥ የአምስቱ ህይወት ማለፉ ታውቋል።

ህይወታቸውን ካጡትም ሦስቱ ወንዶች ሲሆኑ ሁለቱ ሴቶች ናቸውም ተብሏል። በተጨማሪም ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ያካል ጉዳት ደርሶ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ለአደራሹ መደርመስ መንስዔም ከዚህ በፊት አዳራሹ ላይ የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት በከተማው ህዝብ ርብርብ  ጉዳት ሳይደርስበት የተረፈ መሆኑና በጣም ማርጀቱ  እንደ ምክኒያት ተጠቅሷል።

/Ethiopia Nege May 2, 2017/

LEAVE A REPLY