ዶ/ር መረራ ጉዲና ባቀረቡት 11 ገጽ የክስ መቃወሚያ ላይ ዛሬ አቃቢ ህግ...

ዶ/ር መረራ ጉዲና ባቀረቡት 11 ገጽ የክስ መቃወሚያ ላይ ዛሬ አቃቢ ህግ መልስ አሰማ

/Ethiopia Nege News/:- ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዶክተር መረራ ባቀረቡት ባለ 11 ገጽ መቃወሚያ፤ በዋናነት ክሳቸው ከእነ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ክስ ተነጥሎ ሊታይ ይገባል በማለት ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ መልሱን አሰምቷል።

በዚህም አቃቢ ህግ የጋራ ግብ፣ አላማና ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ክሱ ሊነጠል አይገባም ሲል ምላሽ ሰጥቷል። ከዚህ ባለፈም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መተላለፋቸውን በምላሹ ጠቅሷል። በአጠቃላይ መቃወሚያው የወንጀል ስነ ስርዓቱንና ህጉን ያልተከተለ መቃወሚያ መሆኑን በአምስት ገጽ አያይዞ አስተያየት አቅርቧል።

አስተያየቱን የተከታተለው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ዶክተር መረራ ያቀረቡትን መቃወሚያ እና የአቃቢ ህግን አስተያየት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ዶክተር መረራ ጉዲና በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ላይ ባለፈው የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም የክስ መቃወሚያቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY