ኮሚሽነር ዛይድ በህዝባዊው አመጹ የደረሰውን ጥቃት ተ.መ.ድ እንዲያጣራ በድጋሚ ጠየቁ

ኮሚሽነር ዛይድ በህዝባዊው አመጹ የደረሰውን ጥቃት ተ.መ.ድ እንዲያጣራ በድጋሚ ጠየቁ

“የፀረ-ሽብር አዋጁ ልጓም ሊበጅለት፤ የታሰሩትም ሊፈቱ ይገባል።” ኮሚሽነር ዛይድ ራድ አል ሁሴን

/Ethiopia Nege News/:- በኢትዮጵያ መንግስት የተደረገላቸውን የስራ ጉብኝት ዛሬ ሲያጠናቅቁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በህዝባዊ አመፁ” ወቅት የደረሰውን ጉዳት የተ.መ.ድ የባለሙያዎች ቡድን ገብቶ እንዲያጣራ በድጋሚ የኢትዮጵያን መንግስት ጠይቀዋል።

አወዛጋቢው የፀረ-ሽብር አዋጁ ልጓም ሊበጅለትና በህዝባዊ አመፁ ወቅት የታሰሩት ሰዎችም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እያንዳንዳቸው እንዲለቀቁ ሲሉ መንግስትን አሳስበዋል።

ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ዕለት የጀመረው ይኸው የስራ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከተለያዩ የመግስት ባለስልጣናት እንዲሁም 11 ከሚሆኑ የፓርቲ መሪዎች ጋር በመገናኘት፤ ህዝባዊ አመፁን ተከትሎ በተፈጠረው የዜጎች የመብት ጥሰት ዙሪያ መክረዋል።

ኮሚሽነር ዛይድ ራድ ትናንት ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር ሲገናኙ፤ ማዕከላዊ የሚገኙት ዶክተር መረራን ለማግኘት ፍላጎት ቢኖራቸውም ማግኘት እንዳልቻሉ ታውቋል።

LEAVE A REPLY