ጁባ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን አሰረች

ጁባ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን አሰረች

/Ethiopia Nege News/:- የደቡብ ሱዳን የደህንነት ባለስልጣናት ስድስት የሚሆኑ “የኢትዮጵያ የአንድነት አርበኞች ግንባር ” አማፂያንን በህገ-ወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ ግዥ ሰበብ ትናንት ጁባ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

ዘገባው እንደሚያመለክተው ከደቡብ ሱዳን መንግስት እውቅና ውጭ ከአካባቢው ሚሊሽያዎች ጋር የመሳሪያ ግዥ ስምምነት መደረጉ የእስራቱ ምክንያት መሆኑን ያስረዳል።

የንቅናቄው መሪ የሆኑት ጀነራል ቶውት ፖል ቾይ ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ለቡድኑ አባላት መታሰር የቃል አቀባዩ ፖል ኦጁሉ እጅ አለበት በማለት የወቀሱ ሲሆን የቡድኑ ቃል አቀባይ በበኩሉ እጄ የለበትም ይልቁንም መሪው እራሱ ከደቡብ ሱዳን እውቅና ውጭ ያደራጃቸው ናቸው በማለት አስረድቷል።

ከተመሰረተ አስር ዓመታት ያስቆጠረና መሰረቱን በኤርትራና ደቡብ ሱዳን ያደረገ የኢትዮጵያን መንግስት በነፍጥ የሚታገል መሆኑን ዘገባው ያትታል።

ከዚህ ቀደም በርካታ የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን ደቡብ ሱዳን አሳልፋ ስትሰጥ መቆየቷ የሚታወቅ ሲሆን ለአብነትም ኖርዌጂያን ዜግነት ያላቸውን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ተላልፈው ተሰጥተው 9 ዓመት የእስር ቅጣት ተላልፎባቸው በእስላይ ይገኛሉ።

1 COMMENT

  1. Greetings! Very useful advice in this parfticular post! It’s the little changes
    which will make thhe greatest changes. Thanks a lot for
    sharing!

LEAVE A REPLY