/ሙሉ ቃለ ምልልስ/ “ይህ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት አደጋ ላይ የወደቀበት ጊዜ ነው……” ቴዲ...

/ሙሉ ቃለ ምልልስ/ “ይህ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት አደጋ ላይ የወደቀበት ጊዜ ነው……” ቴዲ አፍሮ /

በመጀመሪያው ቀን ለአራት ሰአታት አልበሙ ከሽያጭ ወርዶ በርካታ ስለኮቸን አስተናገደናል /ሲዲ ቤቢ/
/Ethiopia Nege News/:- ቴዲ አፍሮ “ኢትዮጵያ’’ የተሰኘው አዲስ አልበም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በዓለም አቀፍ የሙዚቃ ሽያጮችን በማውጣት በሚታወቀው ቢል ቦርድ የሽያጭ ሰንጠረዡን እየመራ ነው። የሙዚቃ ስራውንና እንድምታውን በተመለከተ ከቪ.ኦ.ኤ.ዋ ጋዜጠኛ ጸዮን ግርማ ጋር ሰፊ ውይይት አድረጓል።

በሦስት ሳምንት የሽያጭ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚለው ነጠላ ዘፈን ብቻ 3,282,095 ተመልካቾች በዩቲዩብ የተከታተሉት ሲሆን ሙሉ አልበሙ ደግሞ በቢልቦርድ ሰንጠረዥ ደረጃውን እየመራ ይገኛል፡፡ በሲዲ ሽያጭ 600 ሺ ቅጂዎችን መሰራጨታቸው ዘገባዎች ያስረዳሉ።

ቴዲ አፍሮ በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ስለ አዲሱ ስራውና ተያያዥ ጉዳዮች ቃለ- ምልልስ ያደረገ ሲሆን። በVOA ከጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር ቃለ ምልልስ አድረጓል።

“..ይህ ጊዜ ኢትዮጵያዊነት አደጋ ላይ የወደቀበት ጊዜ ነው….ይህን ለማዳን ሁላችንም በሀላፊነት መስራት አለብን” ሲል የተደመጠው ቴዎድሮስ ካሳሁን “…ይህን መወደድ የሚሰጥ እግዚአብሄር ነው። ሲልም አምላኩን ሲያመሰግን ተደምቷል። ‘’…ይህ ድምጽ ደግሞ የትውልዱ ድምጽ ነው፣ የጋራ ዜማ ” ሲል ስራውን በአጠቃላይ የህዝብ የስራ ውጤት ነው ሲልም ቴዲ አፍሮ በቃለ ምልልሱ ተናግሯል።

የቴዲ አፍሮን አዲስ አልበም ሲዲቤቢ በመባል የሚታወቀው የጥበብ ስራዎችን በኢሌክትሮኒክስ መንገድ በመሸጥ የሚታወቅ ካምፓኒ ለኢትዮጵያ ነገ በስልክ እንደገለጸው በመጀመሪያው ቀን ብቻ በርካታ ሲዲዎች በአለም አቀፍ ድረጃ እንደሸጠና በዚሁ በአንደኛ ቀን የቴዲ ማኔጅመንት ባልታወቀ ምክንያት ለአራት ሰአታት ከሽያጭ በማውረዳቸው በርካታ የስልክ ጥሪዎችን ሲያስተናግድ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።

/Ethiopia Nege May 10, 2017/

LEAVE A REPLY