በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC) አስራር ውስጥ የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት መኖሩ ይፋ ወጣ

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(EBC) አስራር ውስጥ የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት መኖሩ ይፋ ወጣ

/Ethiopia Nege News/:- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ ላይ ኮርፖሬሽኑን በተመለከተ፤ ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይ የተሰጡትን የም/ቤቱን ሀሳብ  መርምሮ የውሣኔ ኃሣቡን እንዲያቀርብ ለባህል ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኃላፊነቱን ሰጥቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን  ቋሚ ኮሚቴም በበኩሉ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አሁን ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ የተመለከተ አጭር ማብራሪያ ካቀረበ በኋላ ኮርፖሬሽኑ በአስቸኳይ እንዲያስተካክላቸው ያላቸውን ነጥቦች ዘርዝሮ የውሣኔ ኃሣቡን አሳልፏል።

በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በምሰራቸው ሥራዎች ምክንያት የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችና ከተቋሙ ውጪ ባሉ ሰዎች ይደርስብኛል የሚለውን ጣልቃገብነትና ጫና እንደዲያስወግድና ራሱ ያወጣውን ኤዲቶሪያል ፖሊሲና መርህ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለበት የውሣኔ ኃሣብ ተሰጥቶታል።

ኮርፖሬሽኑ ሲገመገምና ሲፈተሽ የመንግሥትንም ሆነ የህዝብን ፍላጐት ማርካት እንደተሣነው ቋሚ ኮሚቴው ያገኛቸው አስተያየቶች እንደጠቆሙት አስታውሶ ይህን አስቸጋሪ ልማዱን እንዲያስወግድ የውሣኔ ኃሣቡን ለኮርፖሬሽኑ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ውስጥ የተሰራፋውን የዝምድናና የቤተሰብአዊ የሥራ ግንኙነት እንዲሁም ጥቅመኝነት የታየ ጉልህ ችግር መሆኑ ስለታመነበት የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎችን አንዲወስዱና “በኤዲቶሪያል ፖሊሲው” ብቻ የሚመራ ተቋም እንዲሆን  የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሣኔ ኃሣቡን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።

ይሁንና በርካታ አስታያት ሰጭዎች የምክር ቤቱን አስተያየት በጥርጣሬ ተመልክተውታል። ምክንያታቸው ደግሞ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መካከል የተፈጠረው አንዱ ቡድን፤ በዶክተር ደብረፅዮን ገብሬሚካኤል የቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራውን አዲሱን ENN(Ethiopia News Network) ተብሎ የሚጠራውን ቴሌቪዥን ተቋም EBCን አኮስሶ ENNን ለማሳደግም ሊሆን እንደሚችል ሀሳብ የሰጡ በርካቶች ናቸው።

ይህንን የመሰሉ ህዝብ ለአመታት አስተያት ሲሰጥበትና ተቋሙ በገዥው ቡድን ያለበትን ጫና በግምገማ ሰበብ  አንድ ቡድንን ለማጥቃት ያሴረ ኃይል መኖሩን የሚያመላክት ነው የሚሉ ሌሎች አስተያየት ሰጭወችም ደግሞ የተቋሞችና የግለሰቦች መጠላለፍ ሳይሆን ሃገራዊ የስርአት ለውጥ ለሁሉም መፍትሄ እንደሚሆን አስምረውበታል።

/Ethiopia Nege May 11, 2017/

LEAVE A REPLY