ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መሃከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲካሔድ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት...

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መሃከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲካሔድ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት ተበተነ!

/Ethiopia Nege News/፦ የህዳሴውን የሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በተመለከተ በሶስቱ ሀገራት መካከል በአዲስ አበባ ለ14ኛ ጊዜ ለሁለት ቀናት ያህል ሲካሔድ የቆየው  ከሶስቱ ሀገራት የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ውይይት ያለውጤት መበተኑን MEMO የተባለ የድህረ ገፅ ጋዜጣ ዛሬ ዘግቧል። የሶስቱ ሀገራት  የቴክኒክ ባለሙያዎች  በዋናነት ግድቡ “በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ” ዙሪያ ያጠነጠነና በግብፅ የመስኖ ሀብት ሚኒስቴር በኩል የቀረበውን ሀሳብ ኢትዮጵያ ውድቅ ማድረጓን ይኸው ጋዜጣ ዘግቧል።

በ2015 የሶስቱ የሀገራት መሪዎች ግድቡ “በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት” ላይ ሊያመጣ የሚችለው ተፅዕኖ ካለ በአለም አቀፍ የዘርፉ ባለሙያዎች እንዲጠና በተስማሙት መሰረት ለሁለት   “የፈረንሳይ ኩባንያዎች” ተሰጥቶ  በማጥናት ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ይኸው የጥናት ቡድን በመጨረሻው “ሪፖርት” ላይ ለመምከር ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ መክሯል። ሪፖርቱን በስድስት ወር ውስጥ አጠናቆ ያስረክባል ተብሎም ይጠበቃል።

 ግብፅ ግድቡን ተከትሎ በናይል ወንዝ የማገኘው አመታዊ የውሃ ድርሻየ ይቀንሳል የሚል ጠንካራ አቋም እንዳላት የሚታወቅ ነው።

 /Ethiopia Nege May 11, 2017/

LEAVE A REPLY