ብትኖርስ የታለህ? /ገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ/

ብትኖርስ የታለህ? /ገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ/

የሆነልህ ቀርቶ በግድ ይሁን ያልከው ከሆነ በኋላ
እንዳይሆን ሁኖብህ እንዳይጠፋህ መላ
ከሆነልህ ጋራ ቀድመህ አትጣላ ።

===================

አይሆነኝም ብለህ የሚሆንህን ሰው
ይሆነኛል ያልከው የማይሆንህ ሲሆን እንዳታስታውሰው
ግብዝ ህሊናህን ፀፀት እንዳይወርሰው
ለጊዜ ተውለት አብሮህ የኖረውን ቀድመህ አታፍርሰው ።

===============[[======

በሆይሆይታ ግፊት በችኩል ውሳኔ
ባልበሰለ እይታ ባልተገራ ወኔ
ልክ አይደለም ብለህ ልክነት ያለኔ
ልኩን አሳይቶ
ልክ እንዳያገባህ የራስህ ጭካኔ
አስተውል ይሄኔ ።

በስተመጨረሻም
ምንም ብታቅራራ አሸንፍኩኝ ብለህ
ተገልጠሀልና ያልሆንከውን ሁነህ
ካሸነፍከው እጥፍ ተሽናፊ አንተ ነህ
አንተነትህ ሞቶ ብትኖርስ የታለህ?

1 COMMENT

LEAVE A REPLY