ካድሬን ካድሬ እንበለዉ /ከሳዲቅ አህመድ/

ካድሬን ካድሬ እንበለዉ /ከሳዲቅ አህመድ/

ካድሬን ካድሬ ካላሉት አይገባዉም

አሸባሪ፣ገዳይ፣ ገራፊና አሳሪ የሆነዉን ህወሃት ለማዳን በአስራ አንደኛዉ ሰዓት የሚኳትኑ ካድሬዎች የሐፍረት መጋረጃን ገልጠዉ አፋቸዉን ሞልተዉ አቋማቸውን ግልጽ ማድረግ በጀመሩበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ኢትዮጵያ ደርሶ ለመምጣት፣ ከደሃዉ አርሶ አደር ተነጥቆ ለሚሰጥ መሬት፣ ፋብሪካ ክፈቱ ብሎ ህወሃት ገንዘብ ለሚመነትፍበት ዉል የሚማስኑ ሆድ አደር ካድሬዎች በዲያስፖራ ያላቸዉ ስምሪት እየጨመረ በመምጣቱ ለፍርፋሪ ካድሬ መሆንን ካመኑበት እኛም እነርሱን ካድሬ ብለን ለመናገር ጨዋና አይን አፋር የምንሆንበት ምክንያት የለም።

የካድሬዎች ተግባር

እነዚህ ካድሬዎች ዲያስፖራ ባሉ ተቋማት ዉስጥ በመግባት ሰላም ይነሳሉ። በየስብሰባዉ ንትርክን በመፍጠር ስብሰባዎች ዉጤት አልባ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። አሸባሪዉን ህወሃት መራሹ መንግስት ለመቃወም የሚደረግ የተቃዉሞ ሰልፍ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስብሰባ፣የሰብዓዊ መብት መረገጥ አስመልክቶ መግለጫዎች እንዳይወጡና ወሳኝ መግለጫዎች እንዲኮላሹ በማድረግ፣ ከአጋር የመብት ተማጋቾች በመጣመር የሚሰሩ ስራዎች የፖለቲካ አርጎ በመፈርጅ ያሰናክላሉ፣ ለአምባገነናዊዉ መንግስት ወንጅል ማስተባባበያ በመስጠት ልማት የሚባል አፍዝዝ አደንግዝን በመደርደር የማዘናጋት ስራ ይሰራሉ።

አንድ ለአምስት በሚሉት መጠፈሪያና የስለላ መረብ በያሉበት አገር ለመብት የሚታገሉን ያውናብዳሉ። ባህር ማዶ ባሉ ህወሃት በተቆጣጠራቸዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ልማታዊ መስለዉ  በመስራት ፖለቲካዊ ጥቅምን ለማስከበር ይጥራሉ። ማንኛዉንም ህወሃት መራሹን የሚቃወም እንቅስቃሴ ፖለቲካዊ ብለው በመፈረጅ በየሲቪክ ማህበራትና የእምነት ተቋማት ዉስጥ የማሸማቀቅ ስራ በመስራት ህወሃት የሚጠቅም ፖለቲካዊ ስራ ይሰራሉ። በማህበረሰብ ዉስጥ ዉዥንብር በመፍጠር በመሪና በተመሪ መካከል ክፍፍልን በመፍጠር ማህበረሰቡ ጠንካራ ሆኖ እንዳይወጣና የጋራ አቋም እንዳይኖረዉ ይጥራሉ። አንድ ጠንካራ ኮምኒቲ እንዲከፋፈል፣እንዲሰነጣጠቅ ዳርና ዳር ቆሞ በማራገብ የህዝብን አንድነት ይሸረሽራሉ። በጥቅሉ እነዚህ የአሸባሪው ህወሃት መራሹ መንግስት ተላላኪ፣ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን ህዝብን የከዱ በመሆናቸዉ ክህደታቸዉ ሊታወቅ ይገባል።

የህዝብን መሰረታዊ ጥቅም 26 አመት በኢትዮጵያዉያን ጫንቃ ላይ ለሻገተዉ ህወሃት አሳልፈዉ የሚሰጡ በመሆናቸዉ ካድሬ በሚለዉ መጠሪያቸዉ እነርሱን ለይቶ መጥራቱ (ፕሮፋይል ማድረጉ) መቀጠል አለበት።የአገርን ጥቅም አሳልፎ ለወራሪ የሚሰጥ ባንዳ ከተባለ፤ የህዝብን ጥቅም ለመቀራመት ፍርፋሪ ለመልቀም የሚጥረዉ ካድሬ ተነጥሎ ታዉቆ የካድሬነት ተግባሩን ህዝብ ሊያዉቀዉ ይገባል።

ካድሬዎቹ ለማን ነዉ ሚሰሩት?

የህዝብን የመናገር ነጻነት ለዘረፈ፣የአገርን የመከላከያ ሰራዊት ለአንድ ብሔር ላደረገ፣ላለፉት 26 አመታት ምርጫን ሰርቆ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለነፈገ፣ያገርን ኢኮኖሚ አዳክሞ ያገርን ሐብት በባእዳን አገራት ባንክ ላስቀመጠ፣የህዝብን የመገናኛ ብዙሗን ነጥቆ የራሱ በማድረግ ለፕሮፓጋንዳ ለተጠቀመ፣የንጹሗንን ደም በማፍሰስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በጥልቅ ሐዘንና ሰቆቃ ዉስጥ ላስገባ፣በወንድ ልጅ ብልት የዉሃ እቃ አንጠልጥሎ ወንድን ያኮላሸ፣ሴት ልጅን እርቃን አርጎ አስገድዶ ለደፈረ፣ በወንድ ልጅ የሰገራ መዉጫ ብረት ሰዶ ወንድን በሽተኛ ያደረገ፣ወጣቱ ካገር እንዲሰደድ አድርጎ በባህር እንዲሰጥም ወይም በበረሃ አዉሬ እንዲበላ ያደረገ፣ በስደት አረብ አገር የደረሰዉን ካድሬዎችን ልኮ ረብሻን በመፍጠር ስደተኞች ታፍሰዉ እንዲመለሱ ያደረገ፣ያገርን መሬት ቆርሶ ለሱዳን  የሰጠ፣ኢትዮጵያን ጨለማ አድረጎ መብራት ለጎረቤት አገር ሽጦ የዉጭ ምንዛሪን በመዝረፍ በዉጭ ባንክ ያስቀመጠ፣ በሙስሊሙም በክርስትናዉም የእምነት ተቋም ዉስጥ በመግባትና ተቋማቱን በመዝረፍ የራሱን ሰዎች ያስቀመጠ፣መጤ አንጃን በእምነት ተቋም አምጥቶ የጫነ፣ ነጋዴዉን በቀረጥ አራቁቶ ያንድን ብሔ ነጋዴዎች እንዲከብሩ ያደረገ፣የተነሳበትን አላማ ለማስፈጸም ትግራይን ለማስገንጠል ጠንክሮ የሚሰራና በአገሪቱ ዉስጥ እንደማፍያ ተደራጅቶ የሚሰራ፣ መንግስታዊና የግል የሆኑ ምስጢራዊ እስር ቤቶችን መስርቶ በአፈና ተግባር ላይ የተሰማራዉን አሸባሪ ስርዓት ትንሽ ፍርፋሪ በመቀበል የከሸፈዉን ስርአት ለማቆየት የሚሹ የዲያስፖራ ካድሬዎች እራሳቸዉ ለራሳቸው በሰጡት የክብር ስማቸዉ “ካድሬ” ተብለዉ ሊጠሩ ይገባል።

የሐሳብ ልዩነት ወንጀል ሲሆን 

የፖለቲካ ተቃዉሞ በሌለበት፣ ፖለቲከኞች በታሰሩበት፣ ጋዜጠኞች በታሰሩበት ወይም በተሰደዱበት አገር ዉስጥ ይህ መርዛማ ስርዓት እንዲቀጥል የሚሻ የዲያስፖራ ካድሬ የማንነት ማእረጉን ሊያገኝ ይገባል። የብሔር ብሔረሰቦች መብት በሚሉት ህዝብን ማከፋፈያና ማስፈራሪያ የከፋፍለህ ግዛዉ መርህ ዉስጥ ተመልምለዉ የሚያሽቃብጡ ዝናቸዉና አሳፋሪ ተግባራቸዉ ይፋ ተደርጎ የሚቀመጥበት የመረጃ ድረ-ገጽ ቢኖር ህዝብ ብስሉን ከጥሬዉ ለይቶ ሊጠነቀቅ እንደሚችል አያጠራጥርም።

የህሊና ጥያቄከናዚ ጋር መተባበር ይቻላልን?

ህዝብ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅና በአፋኝ ኮማንድ ፖስት እግር ተወርች ተጠፍሮ ነዉ ያለዉ።ጥያቄዉ ህሊና ቢስ ካድሬዎችን የማንቃትና እነርሱንም ነጻ ማዉጣት ነዉ። በዘር ጥላቻ ናዚ ከተወገዘ፣ በዘር ጥላቻ ፖለቲካዊ መሰረትን የገነባዉ ህወሃት ሊወገዝ ይገባዋል። በዘር ማጥፋት ወንጀል ናዚ ከተወነጀለ፣አማራን፣ኦሮሞን፣ኦጋዴንንና አኝዋክን  የጨፈጨፈዉ ህወሃት በዘር ማጥፋት ሊወነጀል ይገባል። በመስፋፋትና ጎረቤት አገራትን በመዉረር ናዚ ከተወገዘ፣ ነገ ታላቋን ትግራይ ለመገንባት የወሎን፣ የአፋርን፣የጎንደርን፣ የቤንሻንጉልን መሬት ሰርቆ የህዳሴ ግድብ ገነባለሁ ብሎ የሚንደፋደፈዉ ህወሃት መወገዝ አለብት።

ጥያቄዉ አገርን የማዳን ጥያቄ ነዉ። ጥያቄዉ ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ጥያቄ ነዉ። በአለም አቀፍ ህግ የተከለከለዉን የህገወጥ ገንዘብ ዝዉዉር በማድረግ በዉጭ ባንክ ገንዘብ ከሚያጠራቀመዉ ህወሃት ፍርፋሪን በመቀበል በኢትዮጵያ አየር መንገድ የነጻ ትኬት አንዴ አባቴ አመዉ፣አንዴ እናቴን አመማት፣ አንዴ ድነገተኛ ጉዳይ ገጠመኝ ብሎ ወደ ኢትዮጵያ ተፈትልኮ በህወሃት የመክሸፍ ጠበል ተጠምቆ የሚመጣዉ ካድሬን የሚመለከት ጥያቄ ነዉ።

ካድሬዉነጻነት ባለበት አሜሪካና አዉሮፓ ተደላድሎ የካድሬነት ስራን የሚሰራ ከሆነ ጥፋቱ የመንታፊዉ ህዝብሳይሆን ጥፋቱ የነጻነት ፈላጊዉ ነዉ የሚሆነዉ።

የአዉሮፓ እና የአሜሪካንን ፓስፖርት ይዘዉ አሸባሪ ለሆነዉ የህወሃት መንግስት በካድሬነትና በሰላይነት ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሁላ ያሉበትን አገር ህግ የሚጸረሩ በመሆናቸዉ ካድሬዎቹን ካድሬ” ብሎ ነጥሎ የነሱን ስር መሰረትና ማንነትን የሚያመላክት መረጃን የመሰብሰቡ ስራ መጠናከር እንዳለበት ማሰሰቡ ግድ ይላል። አምባገነናዊና አሸባሪ ለሆነዉ የዉጭ መንግስት (ህወሃት) የሚሰልሉና ንጹሗን ዜጎችን በማስገድልና በማሳሰር የሚተባበሩ ባሉበት አገር ህግ ፊት የሚቀርቡበት ሁናቴ የህግ ባለሙያዎችና የህግ ምሁራን ሊወጡት የሚገባ ሐላፊነት ነዉ።ልብ ያለዉ ልብ ይበል።

LEAVE A REPLY