በኢሬቻ በዓል ላይ ለተከሰተው ተቃውሞ ምክንያት ነበሩ የተባሉ ሁለት ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው

በኢሬቻ በዓል ላይ ለተከሰተው ተቃውሞ ምክንያት ነበሩ የተባሉ ሁለት ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው

ባለፈው ጥቅምት ወር በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታዳሚዎች ፀረ- መንግስት ተቃው ባሰሙበት ወቅት 55 ሰዎች (55 የኢትዮጵያ መንግስት ያመነው ቁጥር ነው) ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

ኢሬቻ በዓል ላይ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ የነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ አካል የነበረ ቢሆንም አመፁን ያስነሱ በሚል ሁለት ሰዎች ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፤ ለ55 ሰዎች ሞት ምክንያት ናቸው በማለት አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል። የፌደራሉ አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው “ ቱፋ መልካና ከድር በዳሶ የተባሉ ግለሰቦች {የኢሬቻ በዓል} በሚከበርበት በወቅት የሀገር ሽማግሌዎች ንግግር ሲያደርጉ ማይክ በመቀማት ሁከትና ብጥብጥ በፍጠር በዓሉ እንዲደናቀፍና በበዓሉ ላይ ታዳሚ ለነበሩ 55 ሰዎች ሞትም ተጠያቂ ናቸው።” ማለቱን አሶሺየትድ ፕረስ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ለመስማት ለግቦት 24/2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY