የፕሮፌ አስራት መቃብር መፍረስ እያወዛገበ ነው! በቅድስተ ስላሴ ካቴድራል እንዲያርፍ እንቅስቃሴ ተጀምሯል

የፕሮፌ አስራት መቃብር መፍረስ እያወዛገበ ነው! በቅድስተ ስላሴ ካቴድራል እንዲያርፍ እንቅስቃሴ ተጀምሯል

ሰሞኑን በማህበራዊ ድህረ-ገጽ ላይ ሲያወዛግብ የሰነበተው የቀድሞ የመአህድ መስራችና ፕሬዚደንት እንዲሁም ታዋቂው የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ መካነ-መቃብር ጨምሮ ሌሎችም በባለወልድ ቤተክርሲቲያን የሚገኙ አጽሞች እንዲነሱለት የባለወልድ ቤተክርስቲያንዋ አሳሰበች፡፡ አጽሙ እንዲነሳ የተወሰነው ቤተክርስቲያንዋ ልማት ለማካሄድ በመፈለግዋ ነው ተብሏል

በዚሁ መሠረት የፕሮፌሰር አስራትን አጽም በስላሴ ቤተክርስቲያን ወደተዘጋጀው ቦታ ማዛወር ስለሚቻልበት ሁኔታ መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ ጥምር ኮምቴ አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ፕሮፌሰር አሥራት የአሁኑ መኢአድ የቀድሞ መአህድ መስራች ሲሆኑ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት በግፍ እስር ላይ እያሉ ያጋጠማቸው ሕመም ወደ ባሰ ደረጃ ከደረስ በሗላ ወደ አሜሪካን ሀገር ሄደው ህክምና እንዲከታተሉ ቢደረግም ህይወታቸውን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቶ ግንቦት በ1991 ዓ.ም ላይ ማረፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ አጽሙን የማዛወር ሁኔታን በተመለከተ በነገው ዕለት በመኢአድ ጽ/ቤት ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሮፌሰር አሥራት የአጼ ሃይለስላሴ የግል ሐኪም እንደነበሩና አጼው በደርግ ቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ጨምሮ ሲያገለግሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡

LEAVE A REPLY