“ከፈተናው ጋር በተያያዘ ኢንተርኔት አልተዘጋም” ትምህርት ሚንስቴር

“ከፈተናው ጋር በተያያዘ ኢንተርኔት አልተዘጋም” ትምህርት ሚንስቴር

/Ethiopia Nege News/;- በአመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ዕሮብ ግንቦት 23/2009 ዓ.ም ድንገት የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት የመንግስት ባለስልጣናትን እያወዛገበ ነው።

የመንግስት ኮምንኬሽን የሰጠው ምክንያት “የኢንተርኔት” በጊዜዊነት የተቋረጠው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ያለውን ፈተና እንደ አለፈው ዓመት እንዳይሰረቅና እንዳይሰራጭ እንዲሁም ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናውን እንዲወስዱ የታሰበ የጥንቃቄ እርምጃ ነው በማለት አቶ ሞሐመድ ሰይድ የተባሉ ባለስልጣን ለሮይተርስ አስረድተዋል።

ዛሬ ደግሞ ትምህርት ሚንስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለዶቸቬለ እንደተናገሩት ኢንቴርኔት የቋረጠው ከፈተናው ጋር በተያያዘ እንዳልሆነና የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳለው “ እኛ ፈተና ይሰረቃል የሚል ስጋት የለብንም።ለመንግስትም ሆነ ለቴሌ እንዲህ አይነት ጥያቄ አላቀረብንም።” ብለዋል።

በሚቀጥለው ሳምንትም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስለሚቀጥል፤ የኢንተርኔት አገልግሎት እስከ ሚቀጥለው ሐሙስ ድረስ እንደ ማይጀምርም ታውቋል።

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አግልግሎት በብቸኝነት የሚያቀርበው የመንግስት ንብረት የሆነው “ኢትዮ ቴሌኮም” ሲሆን በጥራት መጓደልና በክፍያ ውድነት ተጠቃሚዎች እጅጉን ያማርራሉ።

LEAVE A REPLY