የዶክተር መረራ የፍ/ቤት ውሎ

የዶክተር መረራ የፍ/ቤት ውሎ

/Ethiopia Nege News/:- የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፤ በዶክተር መረራ ጉዲና መዝገብ የተከሰሱት ኢሳት(ESAT)ና ኦ ኤም ኤን(OMN) የዜና ተቋማት ላይ የተመሠረተዉ ክስ እንዲሻሻል ዛሬ አዘዘ።

የዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቃ ለችሎቱ በፅሁፍ ያቀረቡትን ቅሬታ ተቀብሎ ብይን ለመስጠት ሌላ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን የተሰየመው ችሎትም የቀድሞዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር፤ የዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቃ ያቀረቡትን ቅሬታ ተቀብሎ ብይን ለመስጠት ሌላ ቀጠሮ ለሰኔ 16/2009 ሰጥቷል።

ጠበቃዉ እንደሚሉት “ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ቢሮ ” የተላከው የፁሁፍ ማስረጃ ደንበኛየ በአሸባሪነት ሳይከሰሱ በአሸባሪነት የተከሰሱ የሚያስመስል መረጃ አቃቤ ህግ መቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውመዋል።

ዶክተር መራራ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተላለፍ፤ከዶክተር ብርሀኑ ነጋ ጋር መገናኘትና OMN ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ መገኘት በሚል ክስ ቀርቦባቸው ከህዳር 2009 ዓም ጀምሮ በእስር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY