ኬንያ 40 ኢትዮጵያንን በቁጥጥር ስር አዋለች

ኬንያ 40 ኢትዮጵያንን በቁጥጥር ስር አዋለች

/Ethiopia Nege News/፦ ትናንት በምስራቅ ናይሮቢ ልዩ ስሙ “ካዮሌ” በተባለ ቦታ 40  ኢትዮጵያንን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው  በአንድ ቤት ውስጥ  እንዳሉ መሆኑን የሀገሪቱ የዜና ተቋማት ዘግበዋል።

የአካባቢው ፖሊስ ኮማንደር እንዳሉት “ኢትዮጵያኑ ወደ ኬንያ ለመግባት የሚያስችል ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ የላቸውም። እድሜቻውም ከ10 እስከ 25 ነው::”  በማለት አብራርተዋል።እንግሊዝኛም ሆነ  ኪስዋህሊ ስለማይናገሩ ለመግባባት ተቸግረው እንደነበረ የገለፁት ኮማንደሩ በአስተርጓሚ  እንዳነጋገሯቸውና  ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ለደላላ ገንዘብ እንከፈሉና ጉዞውን እንዳመቻቸላቸው መናገራቸውን ተገልጿል።

 ዳላሎቹ በፖሊስ እየተፈለጉ እንደሆነና  እስረኞችም ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ የአካባቢው  ፓሊስ አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ብዙ ኢትዮጵያዊያን  ወደ ደብቡ አፍሪካ ለሚያደርጉት ጉዞ ኬንያን  እንደመሸጋገሪያ ሲጠቀሙ በፖሊስ በመያዝ ለእስር እንደሚዳረጉ ይታወቃል።

 /Ethiopia Nege  June 8, 2017/

LEAVE A REPLY