የሰው ህይወት እያለቀ ነው-መንግስተ የምግብ እጥረት እንዳጋጠመው አመነ

የሰው ህይወት እያለቀ ነው-መንግስተ የምግብ እጥረት እንዳጋጠመው አመነ

/Ethiopia Nege News/:- ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ወር ጀምሮ ለድርቅ ተጎጅዎች ለምታደርገው እርዳታ እጥረት እንደሚያጋጥማት አስታወቀች። ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ለሚደረግ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል “የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ” ሹም የሆኑት ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ለአሶሼትድ ፕሬስ ገልፀዋል።

በአሁኑ ሰዓት የአስቸኳይ ጊዜ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 7.8 ሚሊዮን መድረሱንና ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚሆን “ከአንድ ቢሊዮን ዶላር” በላይ የሚሆን ገንዘብ ኢትዮጵያ እንደምትሻ ኮሚሽነሩ አክለው ገልፀዋል።

በወቅቱ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ባለፉት አራት ወራት ብቻ በሁለት ሚሊዮን ማሻቀቡንና እንስሳትም በከፍተኛ ሁኔታ እየሞቱ እንደሆነ አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባው አስታውሷል።

በአማራ፣ ኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች በአንዳንድ ቦታዎች ድርቁ ተባብሶ መቀጠሉንና በርካታ ሚሊዮን ኢትዮጵያ በምግብና ውሃ እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን አይነት ተደጋጋሚና በየአመቱ የሚከሰት የርሃብ አደጋ በተመለከተ መንግስት ፈጣን ምላሽ ካለመስጠቱ የተነሳ የሚከሰት አደጋ መሆኑን የሚገልጹ አስተያየት ሰጭዎች አሁንም የርሃቡ አሳሳቢነት የሰው ህይዎትን እየቀጨ ለመሆኑ አመላካች መረጃዎች እንዳሉ ጠቁመው ርሃቡ በተከሰተባቸው ቦታዎች የከብቶችና እንስሳዎች ማለቅ በመንግስት በኩል የታመነው እጅግ ዘግይቶ ነው ብለዋል።

የሰው ህይወት እየጠፋ ነው የሚሉ ታዛቢዎችና አለማቀፍ ተቋማት በተደጋጋሚ ስጋታቸውን ሲገልጹ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን የመንግስት ፈጣን ምላሽ አሁንም ያለቀውን የሰው መጠን ይፋ አድርጎ ለዘላቂ መፍትሄ ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት አስተያየት ሰጭዎቹ አስምረውበታል።

/Ethiopia Nege June 12, 2016/

1 COMMENT

  1. Great beat ! I would like to apprentice whilst you amend your site, how can i subscribe for a weblog website?
    The account helped me a appropriate deal. I had been a little bit acquainted of this your broadcast provided bright transparent
    concept

LEAVE A REPLY