ጎንደር ከተማ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ የሰው ህይወት አጠፋ

ጎንደር ከተማ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ የሰው ህይወት አጠፋ

/ETHIOPIA Nege News/:- በጎንደር ከተማ በተለይም በአዘዞ ክፍለ ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ከቀኑ 6:30 አካባቢ ጀምሮ ለአንድ ሰዓት ያህል በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ በመጣሉ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

ቤቶቻቸው በከባዱ የዝናብ ውርጅብኝ የተጎዱባቸው ሰዎች ቁጥር ባይገለጽም በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ የመደርመስ አደጋ ማስከተሉ ተመልክቷል፡፡

በአካባቢው ነዋሪ ላይ ያስከተለው መጥነ ሰፊ ኪሳራ ከባድ ቢሆንም የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እስከአሁን የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱን ተናግረዋል፡፡

በአገዛዙ ከፍተኛ ጫና ከሚደርባቸው አካባቢዎች “ጎንደር” ዋነኛ ስትሆን በተለይም የዛሬ ዓመት “የወልቃይት የማንነት ኮሚቴዎች”ን በሌሊት ለመያዝ ህወሓት በሞከረበት ወቅት የሰው ይህወት ከጠፋ በኋላ ከገጠር እስከ ከተማ ከፍተኛ ህዝባዊ እንቅስቃሴን ፈጥሯል። ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ሰው በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ሲገደል፤ በሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ ለግፍ እስራት መዳረጋቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY