በእነ ምጻዊት ሴና ሰሎሞን ክስ ተመሰረተ

በእነ ምጻዊት ሴና ሰሎሞን ክስ ተመሰረተ

መዝገቡ በኦሊያድ በቀለ የተከፈተ ሲሆን ሰባት ተከሳሾችን የያዘ ነው።
/Ethiopia Nege News/:- የፈደራሉ አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመለክተው “በጋዜጠኝነት ሙያ ተሰማርተው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ስለ ሃገሪቱ ፖለቲካ ሁኔታ ቃለ መጠይቅ በማድረግ፤ ሁከትና አመጽ የሚያስነሱ ዜና፣ ግጥምና ሙዚቃ በማዘጋጀት ዩ ቱ ዩብ ላይ እንዲጫን በማድረግና የሽብር ተግባር ለመፈጸም በማሴር፣ ማዘጋጀትና ማነሳሳት” የሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው የታወቀ ሲሆን ነገ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19 ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ የሚነበብላቸው መሆኑ ታውቋል።

ተከሳሾች ድምጻዊት ሴና ሰሎሞንን ጨምሮ ሰባት ግለሰቦች ሲሆኑ
1ኛ ተከሳሽ ኦሊያድ በቀለ
2ኛ ተከሳሽ ኢፋ ገመቹ
3ኛ ተከሳሽ ሞይቡሊ ምስጋኑ፣
4ኛ ተከሳሽ ቀነኒ ታምሩ
5ኛ ተከሳሽ ሃይሉ ነጮ
6ኛ ተከሳሽ ሴና ሰለሞንና
7ኛ ተከሳሽ ኤልያስ ክፍሉ ናቸው።
ባሳለፍነው ሳምንት ምጻዊት ሴና ሰሎሞን ጨምሮ ሌሎች ሶስት አርቲስቶች ከ6 ወር በላይ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማእከላዊ እንደሚገኑ ተዘግቦ እንደነበረ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY