ሳውዲ የምህረት አዋጅ ተራዘመ

ሳውዲ የምህረት አዋጅ ተራዘመ

/Ethiopia Nege News/:- የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጪ ሐገር ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው አንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ- ገደብ ባለፈው እሁድ መጠናቀቁ ይታወቃል።

በብዙዎች ግምት በሳውዲ ለመኖር የሚያስችል ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ከአራት መቶ ሺህ እንደሚልቅና ከነዚህም ውስጥ 45000 የሚሆኑት አዋጁን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሱ የኢትጵያ መንግስት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከአንድ ወር በፊት በይፋ የምህረት አዋጁ እንዲራዘም መጠየቁ የተነገረ ቢሆንም አዋጁ ከተጠናቀቀ ከአስት ቀናት በኋላ ዛሬ ለአንድ ወር ማለትም እ.ኤ.አ ሐምሌ 24/2017 ድረስ መራዘሙን የሳውዲ የሚዲያ ተቋማት ዛሬ ማምሻውን ዘግበዋል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የጉዞ ሰነድ ከወሰዱት 85 ሺህ ዜጎች መካከል ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት ከቁጥራቸው በጣም አነስተኛ እንደሆነ ይገልፃሉ። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቅሱት አገዛዙ በሚፈፅመው የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና በማህበራዊ ህወታቸው ላይ በሚፈፀምባቸው “አድሏዊ” አሰራር እንደሆነ ተመላሾቹ አበክረው ይናገራሉ።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደባት ወደ አለችው “የመን” የሚሸሹት ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው እየጨመረ መሄዱ ጉዳዩ የበለጠ አሳሳቢ እንደሆነ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY