ሳውዲ አረቢያ 12 ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን በቁጥጥር ስር አዋለች

ሳውዲ አረቢያ 12 ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን በቁጥጥር ስር አዋለች

/Ethiopia Nege News/:- አመት በፊት በይቅርታ 1438ኛውን የኢድ አልፈ-ጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ “የሐጅና ኡምራ” ሀይማኖታዊ በአል ላይ ለመካፈል ወደ ሳውዲ አረቢያ የተጓዙት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ በሳዉዲ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለፈው ሐሙስ ሌሊትና አርብ በሳውዲ ፖሊሶች መታሰራቸው ታወቀ።

የረመዳንን የጾም ፍች ምክንያት በማድረግ በሳውዲ አረቢያ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊም ኢትዮጰያውያን ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ ከተሳተፉ በኋላ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ዶክተር ጀይላን ከድር፣ኢንጂንየር በድሩ ሁሴንና ሌሎች ቁጥራቸው 12 የሆኑ ኢትዮጵያዊያን እስካሁን ባልታወቀ ምክንያት በሳውዲ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

ታሳሪዎቹ በፖሊስ ተይዘው ወደ ሳውዲ አረቢያ የደህንነት መስሪያ ቤት ከተወሰዱ በሗላ ቅዳሜ እለትደግሞ ጅዳ “ሀያልሳህመር” ወደ ተባለ ወህኒ ቤት መዘዋወራቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል።

የሳውዲ አረቢያም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ያሉት ነገር አለመኖሩ ታውቋል።

ከ6 ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሙ ማህበረሰብ “የመጅሊስ አመራሮች የሕዝበ ሙስሊሙ ውክልና

የሌላቸው በመሆኑ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ በነጻነት በሚመረጡ አመራሮች ይተኩልን፤ በመጅሊሱ አማካኝነት በኢትዮጵያ

ሙስሊሞች ላይ በግድ እየተጫነ ያለው የአህባሽ የማጥመቅ ዘመቻ ይቁምልንና አወሊያ መንፈሳዊ ት/ቤት የህዝበ ሙስሊሙ ነጻ ተቋም

ሆኖ እንዲቀጥል መጅሊስ እጁን ከአወሊያ ያንሳ” የሚሉ ጥያቄዎች በተነሱበት ወቅት መንግስት ጥያቄውን ኮሚቴ ምረጡና እንደራደር ባለው መሰረት፤ አቡበከር አህመድን ጨምሮ 17 አባላት ያለው ኮሚቴ ተመርጦ ከመንግስት ጋር ድርድር ከተጀመረ በኋላ መንግስት ኮሚቴዎቹን በሽብር ከሶ እስከ 22 ዓመት ድረስ በእስራት ከቀጣ በኋላ ከአንድ መፈታታቸው ይታወቃል።

LEAVE A REPLY