በሳውዲ አረቢያ ታስረው የነበሩት ኡስታዞች ከእስር ተፈቱ

በሳውዲ አረቢያ ታስረው የነበሩት ኡስታዞች ከእስር ተፈቱ

/Ethiopia Nege News/:- ኢትዮጵያኑ የሀይማኖት መሪዎች በኡምራ ሀይማኖታዊ በአል ላይ ለመካፈል ወደ ሳውዲ አረቢያ አቅንተው፤በጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ባዘጋጁት “የክብር መግለጫ” ፕሮግራም ላይ ከተሳተፉ በሗላ ሐሙስ ሌሊትና ቅዳሜ እነ አቡበከር አህመድን ጨምሮ 12 ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

በጅዳ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያን ምንጮቻችን እንደነገሩን ከሆነ “ኡስታዞቹ ለእስር የተዳረጉት በጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ለኡስታዞች ወይም ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ በመካፈላቸው ህገ-ወጥ ስብሰባ አደረጋችሁ ተውብለው በሳውዲ ፖሊሶች እንደታሰሩ” ገልፀውልናል። ከአንድ ሳምንት እስራት በሗላ ዛሬ ሁሉም እንደተፈቱ ታውቋል።

ቢቢኤን በበኩሉ የሚከተለውን በፌስቡክ ገጹ ላይ ለጥፏል

“በጅዳ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ታስረዉ የነበሩት ኡስታዞች፣ዳኢዎችና ኡለሞች ከእስር መፈታታቸዉን ቢቢኤን ጅዳ ካሉት ምንጮቹ ደዉሎ ለማረጋገጥ ችሏል። ለኡምራ ስነስርዓት ወደ መካ የተጓዙት ኡስታዞችና ዳኢዎች ጅዳ ዉስጥ በተካሔደ የኢድ ስነ ስርዓት ላይ እንግዳ ሆነዉ በሔዱበት በድንገት መታሰራቸዉ ይታወሳል። ከቀናት እስር በሗላ ዛሬ ሁሉም መፈታታቸዉ ተረጓግጧል።

ለአመታት የኢትዮጵያዉያንን ሙስሊሞች ድምጽ ለማሰማት እስር፣ መከራና ስቃይን የተሸከሙት እነዚሁ ኡስታዞች ከሚወዳቸዉና ከሚናፍቃቸዉ ቤተሰብ ጋር በሰላም ይቀላቀሉ ዘንድ ዱዓችን (ጸሎታችን) ነዉ።”

LEAVE A REPLY