ጋንተ ዲብ – የሽንሌ አፈነ – እጅ ስጥ /ታሪኩ ደሳለኝ/

ጋንተ ዲብ – የሽንሌ አፈነ – እጅ ስጥ /ታሪኩ ደሳለኝ/

ኦሪያ ጋንተ ዲብ (እጅ ስጥ) ይህን ቃል ከሠላሳ በላይ ባለጠብ-መንጃ ወታደር ከተኮሰተረ ፊት ጋር በምሽት ዙሪያህን በሦስት ፒካፕ የወታደር መኪናና በአንድ ድፌንደር መኪና ተከበህ መሳሪያ እየተቀባበለብህ መሰማት መናገር በማትችልበት ቋንቋ ከዚህም ከዚያ “ጋንተ ዲብ” እጅ ስጥ ስትባል ምን እንደሚሰማህ አስበው? ግራ በመገባትና ከአሁን አሁን ምን ሊፈጠር ነው ብለህ እየጠበቅን ከወታደሮቹ ጋር ስንተያይ ድንገት ከመሀላቸው በግማሽ አማርኛ በንዴት አንዱ አፍጥጦ እያየን “

እዚህ ምን ልትሰሩ መጣችሁ? እዚህ ምንድነው የምትሰሩት” አለን “በመጀመሪያ እዚህ የመጣነው ሀገራችን ስለሆነ ነው…..” ከማከቴ በወታደር ጫማ ከጉልበቴ ስር ተመታሁ ሌሎችም ወታደሮቹ በያዙት ዱላ ባገኙት ነገር ወንድ ሴት ሳይሉ እየተማቱ በከፍተኛ እንግልት ፒካፕ መኪናቸው ላይ ወረወሩን …..ወታደሮቹ ፒካፕ መኪና ላይ ከጫኑን በኃላ 12 ኬ.ሜ እርቀትን በ160 የመኪና ፍጥነት በፒስታ መንገድ ላይ እየከነፉ ወደ አንድ ግቢ አስገቡን። ግቢ ውስጥ እንደገባን ከመኪናው ላይ እየጉተቱ ከወረዱን በኃላ የያዘነው እቃ ፊት ለፊት እንድናስቀምጥ ካደረጉን በኃላ በየተራ እያስቆሞ እያመናጨቁ ፈተሹን ወንዶች ለብቻ ሴቶች ለብቻ ካደረጉን በኃላ የመጡት ወታደሮች ሁሉ ከ10 ጊዜ በላይ ቆጠሩን። ይሄ ሁሉ ሲሆን እንድናወራ አልፈቀዱልንም እራሳቸው ይጠይቃሉ እራሳቸው ይመልሳሉ ደግሞ ይጮሀሉ።

ከቆጣራና ከፍተሻ በኃላ ወንዶችን በሦስት መስመር እንድንቀመጥ አደረጉን ወደ ፊታችን ሁለት ሰዎች መተው ቆሙ አንደኛው የእጅ ሽጉጥ የያዘ ሲሆን ሁለተኛው ሽመል ይዞል እነዚህ ሰዎች ከመጀመሪያው ጀምሮ በነሱ ትእዛዝ የያዘነው ንብረቶች እየተወረው መኪና ውስጥ እንዲገባ እና እኛም ተጭነን እንድንመጣ ትእዛዝ ሲሰጡ የነበሩት ግለሰቦች ናቸው። ባለመሳሪያው የአካባቢው የፀጥታ ክፍል ሀላፊ ሲሆን ባለሽመሉ የፖሊስ ኮሚሽን ነው። ሁለቱ ሰዎች ወደኛ እንደቀረቡ ወታደሮቹም ዙሪያችን ከበው እጃቸውን የመሳሪያቸው መላጭ ላይ አደረጉ …..

ይህን ድርጊት የተፈፀመው ትላንት አርብ ሰኔ 30 /09ዓ.ም ከአዲስ አበባ 592 ኬሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኘው የሱማሌ ክልል በሆነችው ሽንሌ ወረዳ (ድሬደዋ ኬላ) ከምሽቱ 1:20 ላይ ነው። ድርጊቱን ፈፃሚው የሱማሌ ክልል ወታደሮች ሲሆኑ ድርጊቱ የተፈፀመብን “የዘመን ድራማ” ሙሉ የፕሮዳክሽን አባለት ላይ እና የድራማው የስደቱ ክፍል የሚጫወቱት ተዋንያኖች ላይ ነው።

ሁለቱ ሰዎች ፊታችን እንደቆሙ አስተርጓሚ መርጠው የሚሉትን እንድንሰማማ እና እንድንናገር አደረጉ የመጣንበትን አሰረዳን ከድሬደዋ አስተዳደርም ፍቃድ እንዳለን አሳየን ከሱማሌ ክልል ከምንሰራበት ሽንሌ ወረዳ እንዳስፈቀድን አ?ስረዳን የፀጥታ ሀላፊው አንድ ስልክ እየደወለ ወደ ኃላ አለ ስልኩን ጨረሷ ወደፊት መጣ በእጁ ምልክት አሳየ ወታደሮቹ መሳሪያቸውን ዝቅ አደረጉ አንድ ቃል ተናገረ ተተረጉመልን “አሁን አውቀናል ሄዱ” ተባልን እንግዲህ ምን እናድርግ ሄደን።
ዘመን ድራማን ለመስራት ወደዚህ ክልል ስንመጣ ለ3ኛ ጊዜችን ነው። ከዚህ ቀድሞ ድሬደዋ ከተማ ላይ በተለምዶ ጀርባ ሠፈር የሚበል አካባቢ ስንሰራ በፖሊስ ስራውን አስቁሙን አርቲስት መስፍን ጌታቸው ወደጣቢያ ተወስዱ ከቆይታ በኃላ ፍቃዳችንን አይተው ተለቋል።

በኢትዩጲያ ውስጥ ማንም እንዳሻው እየተነሳ በየቦታው ስራ የሚያስቆመው የስራ መስክ ቢሆን የፊልም ስራ ነው።

በነገራችን ላይ ድሬደዋ ከተማ በከፍተኛ ውጥረት በተለያየ ቦታ መንገድ ተዘግቷ በወታደሮች እየተጠበቀች ነበር ምክኒያቱም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ስለነበረ ነው። እኛም ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ካለንበት 16 ኬ.ሜ እርቀት ላይ ነበርን። ዳሩ መንግስት የመንግስት ብቻ እንደሆነ ህዝብም ህዝብ እንደሆነ በአንድ ሀገር ሳንተያይ መኖር ከጀምርን 26 አመት አልፎናል።

#ታሪኩ-ደሳለኝደሳለኝ-ዘመን- ድራማ
ሐምሌ1/09ዓ.ም “ሽንሌ”

LEAVE A REPLY