አዲስ አበባ በስራ ማቆም አድማ እየተመታች ነዉ

አዲስ አበባ በስራ ማቆም አድማ እየተመታች ነዉ

/Ethiopia Nege Amharic News/:- መንግስት በግዴለሽነት ያወጣዉ የግርብር አከፋፈል መመሪያ እስኪስተካከል የስራ ማቆም አድማው ይቀጥላል። የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ሰሞኑን አብዛኛውን የኦሮሚያ ክልል ከተሞችን ያሳተፈው የነጋዴዎች ተቃውሞ ዛሬም ተባብሶ በነቀምት፣ አምቦ፣ ጊንጪ፣ አርሲ፣ ሻሸመኔና ሌሎችም አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ አዋሳኝ ከተሞች ሆለታና ቡራዩ የንግድ እንቅስቃሴው ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠ ሲሆን አድማው ወደ አዲስ አበባ ከተማም ዘልቋል።

ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚታይበት ኮልፌ አካባቢ ያሉ ሱቆች በዛሬዉ እለት መዘጋታቸው የታወቀ ሲሆን፤ የስራ ማቆም አድማዉ በስፋት ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት መኖሩንም ከአዲስ አበባ ካነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለመረዳት ችለናል።

በመርካቶ፣ አጠና ተራ፣ መሳለሚያ፣ ሽሮ ሜዳ፣ ሳሪስ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ዘግተው መዋላቸው የታወቀ ሲሆን መንግስት የጣለባቸውን አግባብ ያለልሆነ “የቀን ገቢ ግምት” እስኪስተካከልላቸው የወሰዱትን እርምጃ እንደሚገፉበትም ገልጸዋል።

በተለምዶ 18 ማዞሪያ በመባል በሚታወቀዉ አካባቢ በአነስተኛና ጥቃቅን ማህበር ስር የተደራጁ ነጋዴዎች የተጣለባቸዉን የቀን ገቢ ግምት በመቃወም ለመንግስት አቤቱታ እንዳሰሙ ታዉቋል። ከ1300 እስከ 3000 ብር ታስገባላቹ በማለት በቀን ገቢ ገማቾች ግብር የተጣለባቸዉ ነጋዴዎችን ጉዳዩን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማዉ ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ ቢደረጉም የመፍትሔ ሐሳብ ሳይገኝ ስብሰባዉ በተቃዉሞ መበተኑ ታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሚንኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ ማምሻውን በቪ ኦ ኤ ቀርበው እንዳሉት “ህዝቡ ግብሩን እንደ እዳና ሸክም ማየቱን ትቶ የተጣለበትን ግብር በተያዘለት ጊዜ እንዲከፍል” በማለት በማስጠንቀቂያ አዘል ንግግራቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY