አንድም ሦስቱም መረራ /ዘላለም ክብረት-Zone 9/

አንድም ሦስቱም መረራ /ዘላለም ክብረት-Zone 9/

አፍሪካ ከበደ ገና በአስራዎቹ የዕድሜ መጨረሻ ላይ ያለ ወጣት ነው፡፡ በጣም ተስፈኛ ነው፡፡ ሁሌም ለውጥ እንደሚመጣ መናገር ይወዳል፡፡ ለምን ስሙ ‹አፍሪካ› እንደተባለ ሲጠየቅ ደጋግሞ ወደ መምህር አባቱ ይጠቁማል፡፡ አባቱ ስድስት ልጆች እንዳላቸውና የመጀመሪያዋን ዓለም፣ ሁለተኛውን አፍሪካ፣ ሦስተኛውን ኢትዮጵያ፣ አራተኛዋን ኦሮሚያ፣ አምስተኛዋን ወለጋ እንዲሁም ስድስተኛዋን ደግሞ ሊሙ ብለው ስም እንዳወጡላቸው ለጠየቀው ሁሉ ፈገግ እያለ መናገር አይሰለቸውም፡፡ አፍሪካ በወጣትነት ዕድሜው የትውልድ ከተማው የምስራቅ ወለጋዋ ሊሙ ኮሳ ከተማ ውስጥ የኦሮሞ ፌደራል ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ነው፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር መሆን ብዙ መዘዝ በሚያስከትልበት አገር አፍሪካ በተስፋ ጽሕፈት ቤቱን በራሱ ያቋቋመው ‹የአካባቢው ሰው አማራጭ እንዲኖረው› በሚል ሐሳብ እንደሆነና፤ ከፓርቲው የማረጋጋጫ ፈቃድ ተቀብሎ በጽሕፈት ቤቱ ጊቢ ውስጥ የኦፌኮን አርማ የያዘ ሰንደቅ ዓላማ ከክልሉና ከብሔራዊው ሰንደቅ ጎን የሰቀለ እለት በወረዳዋ የተፈጠረው ትርምስን እያስታወሰ ፈገግ ይላል፡፡ ‹‹አፍሪካ የመረራን ባንዲራ ሰቀለ›› በሚል የወረዳው አመራሮች ተሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተወያይተው ለጥቂት ቀናት ከታሰረ በኋላ በፓርቲው ጥረት ተፈቶ ወደስራ እንደገና አንደተመለሰ ይናገራል፡፡ ‹‹የእኛ ጽሕፈት ቤት መክፈት በወረዳው አመራሮች ለሚበደሉ ሰዎች ትልቅ ተስፋ ሁኖ ነበር›› ይላል አፍሪካ፡፡ እንዲያውም አንዳንዶች የመንግስት ሰራተኞች አለቆቻቸውን ‹‹አላሰራም የምትሉን ከሆነ አፍሪካ ጋር ሒደን እንሰራለን›› እያሉ ያስፋራሩ ነበር ይላል፡፡

ለአፍሪካ የፓርቲው መኖር ትልቁ ትርጉሙ ለዜጎች ተስፋ መስጠቱ ነበር፡፡ ከዚህ ተስፋ ጀርባ ደግሞ አንድ ስምን ደጋግሞ ያነሳል፤ መረራ ጉዲና፡፡ ‹‹ዶክተር ጋር ከደወልኩ የማንፈታው ችግር አልነበረም፡፡ የታሰሩ አባላቶቻችን በአንድ ስልክ ወዲያው ነበር የምናስፈታው›› ይላል መረራን እያወደሰ፡፡ በርግጥም አፍሪካ በወጣትነቱ ተስፋ ስለሰጡት ጎልማሳ መረራ ጉዲና አውርቶ አይጠግብም፡፡

የሦስት ጨቋኞች እስረኛ

መረራ ከ21 ዓመታት በፊት በሚያዚያ 1988 የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስን (ኦብኮ) ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር ሲመሰርቱ የሚጓዙት መንገድ ረጅም እና አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል አልገመቱም ማለት አይቻልም፡፡ በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት ከነበራቸው የፖለቲካ ተሳትፎ አንፃር እንዲሁም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ለአምስት ዓመታት የኢሕአዴግ አካሔድ ትዝብታቸው ነበር ለዚህ ድምዳሜያቸው መሰረቱ፡፡

የንጉሱን አምባገነናዊ ስርዓት እንደ ዕድሜ አቻዎቻቸው በማርክሳዊ መንፈስ ተለክፈው ተቃውመው በመነሳት ገና በአስራዎቹ የዕድሜያቸው መጨረሻ ነበር በትውልድ አካባቢያቸው አምቦ ለመጀመሪያ ጊዜ እስርን የቀመሱት፡፡እስራቸው አጭርና የማያስቆጭ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ እንደማንኛውም የዘመናቸው ወጣት የሶሻሊዝምን ጠበል የተረጩት በዛው ዘመን ነበር፡፡ ‹እኔ› ማለት ትተው ‹እኛ› ማለት የጀመሩበት ዘመን፡፡ መታሰራቸው የፖለቲካ ፍላጎታቸው ጨመረው እንጅ አልቀነሰውም፡፡

መረራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲታሰሩ አዲስ መንግስት ተቋቁሞ የእራሳቸውም የፖለቲካ ተሳትፎ በእጅጉ ከፍ ያለበት ወቅት ነበር፡፡ የመላው ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄን (መኢሶንን) በዩንቨርስቲ የትምህርት ጊዜያቸው የተቀላቀሉት መረራ፤ ፓርቲያቸው ጨካኙን የደርግ ስርዓት ‹ይስተካከል ይሆናል› በሚል ተስፋ እየገሰፀ ለመደገፍ በወሰነው መሰረት ሁለት ዓመታት ያክል በስጋት ከኖረ በኋላ ደርግ ፊቱን ሲያዞርበት እርሳቸውም እንደ ማምለጥም እንደ ሽፍትነትም አሰኝቷቸው ሲሸሹ ከትውልድ ቀያቸው ብዙም ሳይርቁ ተያዙ፡፡ አሁን አልፎ ሲያስታውሱት የፓርቲያቸው አመራሮች ከመዲናዎ ወጥተው ሱሉልታ ላይ መያዛቸውን አስመልክቶ ‹‹የመኢሶን ሽፍትነት ከሱሉልታ አላለፈም›› ለሚሉት መረራ የእራሳቸው ሽፍትነት በመጠኑም ቢሆን የተሻለ ርቀት ተጉዞ ነበር፡፡

የመረራ ሁለተኛ እስር ግን እንደመጀመሪያ ቀላል አልነበረም፡፡ ከሰባት ዓመታት በላይ ታስረዋል፡፡ የታሰሩበትን ምክንያት በውሉ አልተነገራቸውም፡፡ ጓደኛቸው ‹‹ ‹ቀንደኛው ወንበዴው መረራ ጉዲና ከነሙሉ ትጥቁ በቁጥጥር ስር ዋለ› የሚል ፅሁፍ በወቅቱ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ተፅፎ አይቻለሁ›› እያለ ይቀልድብኝ ነበር ይላሉ ስለተያዙበት ሁኔታ ሲተርኩ፡፡ በርግጥም ይህን መሰል ዜናዎች በወቅቱ በርከት ብለው ይታዩ ነበር፡፡ ‹‹ቀንደኛው ወንበዴ አሊ ፋሪስ ከግብረ አበሮቹ ጋር ተያዘ››፤ ‹‹በጢቾ ማማ አብዱልቃድር የተባለ ቀንደኛ ወንበዴ ከነመሳሪያው ተያዘ››፤ ‹‹በጀልዱ ወረዳ በ19 ወንበዴዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወሰደ›› … የሚሉ ዜናዎች የመንግስታዊው ጋዜጣ የፊት ገፅ አድማቂዎች ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን እርሳቸው በታሰሩበት ወቅት የታተሙትን መንግስታዊ ሕትመቶች የፊት ገፆች አስሰን ‹‹ቀንደኛው ወንበዴው መረራ ጉዲና ከነሙሉ ትጥቁ በቁጥጥር ስር ዋለ›› የሚለውን ዜና ማግኝት ባንችልም ግመታው (the claim) ከእውነታው ብዙም የራቀ ነው ማለት አንችልም፡፡

በርግጥ የመረራ የደርግ እስር ቤት የሰባት ዓመታት ቆይታ መረራን እጅግ ቀይረዋቸው ነበር፡፡ እርሳቸው እንደሚሉትም፡

ከአምቦ የተማሪዎች ንቅናቄ ተጀምሮ እዚህ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም አልፌ፣ ሰባት ዓመት ታስሬ ስወጣ በጣም ካልተገፋሁ በስተቀር የጭንቀት ፖለቲካውን ትቼያለሁ፡፡ ትዝ ይለኛል ‹‹ወደድክም፤ ጠላህም መኢሶን ያሸንፋል!…›› እንዲህ ያለ ነገር በወጣትነታችን ጠንከር ባለ መንገድ ተከራክረናል፡፡ በዚያ ውስጥ የተለወጠ ህይወት ነው፡፡ አክርረህ የፈለከውን ያህል ብታቀርብ ዝም ብሎ ውሃ ልኩን አያልፍም፡፡ ስለዚህ፤ የማክረር ፖለቲካውን የተውኩት በተወሰነ ደረጃ በዚያ ሰባት ዓመት እስራት ነው፡፡ በእርግጥ፤ ብዙ ጊዜ ሞት አጋጥሞኛል፡፡ ከአምቦም፤ ደርግ ጽ/ቤትም፣ ቢያንስ ሶስት፣ አራት ግዜ ከሞት በዕድል አምልጬያለሁ፡፡ … ስለዚህ፤ በተለይ ላለፉት 40 ዓመታት የከረረ ፖለቲካችን የትም አላደረሰንም፡፡ ያ ያለፍንበት ሁለመናዬን ለውጦታል … አንዳንድ ግዜ ማክረሩን እየተውክ ስትመጣ ወደ ተፈጥሮ ትሄዳለህ፡፡

መረራ ሁሌ የሚሉት በአገራችን ፖለቲካ የጠፋውን የመሃል መንገድ ያገኙት በእስር ቤት ነበር፡፡ አክርሮ ጫፍ ላይ መቆሙ

LEAVE A REPLY