የጉድ አገር ገንፎ አድሮ ይፋጃል /ዮሃንስ ደሳለኝ-ከጀርመን/

የጉድ አገር ገንፎ አድሮ ይፋጃል /ዮሃንስ ደሳለኝ-ከጀርመን/

ሰሞኑን በአንዳንድ የሶሻል ሚዲያዎች ከኢትዮጵያ ቴሌቭዝን ተወስዶ የተለቀቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግራ የሚያጋባና ሰውየው ለይቶላችዋል ያስብላል። እስቲ አሁን መረጃ በበዛበት ዘመን ያውም የህወሃት የሰለላ መረብ ሳር ቅጠሉ ሳይቀር ጆሮ በሆነበት የመከራ ግዜ ከታች ካሉ ሰዎች መረጃ አይመጣልኝም በግምት ነው የምሰራውና የምወስነው እያሉ መቀባጠር ማንን ለማታለል ይሆን? ሰፊውን፣ በደለኛውንና ሆዱባዶ ሆኖ ሆደሰፊውን ህዝብ ከሆነ አያያያ እኔ ልሙት ተሳስተዋል፣ ሰፊው ህዝብ ከነቃ ሰነባብቷል የእርሰዎ ጅልነትና አሻንጉሊትነት (Puppet)ተረድቶ ከረሳዎት ቆይቷል፣ አይ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር በእውነት አሳዘኑኝ ምክኒያቱም እንደሰለጠኑት አለም መሪዎች መምራት ሰላልቻልኩ ስልጣን ለቅቂያለሁ ማለት ሰላቃተወት ከንቱ ሃሳብ ይዘው ከንቱነትዎን በአደባይ አወጁ።

ይልቅ ይህን የማያዋጣ ቁመራ ትተው ሰሞኑን አስተዳድረዋለሁ በሚሉት ህዝብ ላይ የከመሩትን የግምት ግብር መፍትሄ ለማበጀት ይስሩ፣ ውይ ሞት ይርሳኝ ለካ ረስቸው ርስዎ የት ያውቁትና መረጃ የለዎት አሳዳሪዎቹ ወያኔዎቹ አስፈላጊውንና እድሜያቸውን የሚያረዝመውን ነገር መቼ ይነግሮዎታል እርስዎ ብቻ እንደደህና የእድር ጥሩንባ የተባሉትን መለፈፍ ነው ደግሞ እርግጠኛ ነኝ ሌላ ተጭማሪ አስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንደሚያውጁ ከዚያ የሞተው ሞቶ የተረፈው ተርፎ ርስዎም እየዋሹና እየተጃጃሉ ይቀጥላሉ ።

ለመሆኑ አሁን በአገሪቱ ውስጥ ባሉ በሁሉም የስራ ዘርፍ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ፣በተለይ ደግሞ በአነስተኛ ንግድ ዘርፍ ላይ ያሉትን ዕዳ በዕዳ ማድረግ ተገቢ ነው፣ ከሆነም ደግሞ አግባብ ባለው መንገድ እንጅ እንዴት በየቀበሌውና በየወረዳው የሚገኙት የወያኔ የደህንነት ሰዎች ደጋፊና ተቃዋሚውን እየለዩ የሚመቱበትና የስርዓቱ ደጋፊዎችን ብሎም የአንድ ብሔርን በሁሉም ነገር የበላይ የማድረግ አባዜ አገሪቷን ወደባስ ብጥብጥ ይመራታል እንጅ እናንተ እንዳቀዳችሁት አልጋ በአልጋ የሚሆን ከመሰላችሁ ውጤቱን አብረን የምናየው ይሆናል።

የታክስ ስርዓት ለአንዲት አገር አስፈላጊና አሌ የማይባል ነገር ሆኖ ሳለ ነገር ግን ይሄ ስርዓት ወይም አካሄድ ባለሙያ የሚጠይቅ ብሎም በሙያው ዘርፍ ጥናት ያደረጉ ሰዎችን ያካተተ የሌላውን አገር ተሞክሮ ያዩ ሰዎችን መሰረት አድርጎ ጠቃሚና ጎጅ ጎኑ ተጠንቶ በአግባቡና ስርዓት ባለው መልኩ ለህዝብ ተነግሮ በአዋጅም መውጣት ካለበት ታውጆ መደረግ ሲገባው ቀበሌ ወይም ወረዳ ውሰጥ ያውም በኃላፊነት ቦታ ስይቀመጡ ነገር ግን ባላቸው የስለላና የጆሮ ጠቢነትና ክህሎት የፈለጉትን የሚያጠቁበት ሁኔታ አስገራሚና አሁንም አስተሳሰባችሁ ከጫካው እንዳልወጣ አመላካች ነው ፣የዚህ አስደንጋጭ የግምት ግብር ሁኔታ የሚገርመው ነገር ቢኖር አንዳንዶችሁ በአነስተኛ ንግድ ህርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎች የተጣለባችውን (ሆን ተብሎ ለመጉዳት መሆኑ የሚያስታውቀው) ሲሰሙ ያን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ በንግድ ዘመናችው አለመስማታቸው ነው ፤ ታድያ ይሄ ምን ይሉታል? ጥጋብ ፣ዕብደት፣ ማስተዳደር አለመቻል ፣ወይስ ዕብሪት ሁሉም ለወያኔ ይመጥናሉ።

አንዳንዴ የወያኔ መራሹ መንግስት ባለስልጣኖች ለህግ ያላቸው አመለካከት ይገርመኛል ፣ህግ በተለያዩ አካላት ይወጣሉ በፓርላማ ፣እንዲሁም በባለስልጣን መስሪያቤቶች ምን አለፋችሁ ሁሉም እንደተመቸው ህግ ያወጣል ወዲያው ሌላው ምክኒያቱ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ ይሽራል ሲሻቸው ደግሞ በ24ሰዓት ውስጥ ያውም ህገመንግስትን የሚቀይር ህግ ያወጣሉ ብቻ ምን አለፋችሁ አንድ ወቅት ፕሮፈሰር መስፍን ወ/ማሪያም እንዳሉት በኢትዩጵያ ምድር ህገ አራዊት ከሰፈነ ቆይቷል ፣አገሪቷ ህግ አውጭም አስፈጻሚም የላትም ሁለቱንም የሚያከናውነው ያው ምስጢራዊው የወያኔ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው ።ለዘህም አስረጅ ምክኒያቶችን ብንጠቅስ በአንድ ወቅት (የፈለጉትን ለማሰር )የወጣውን የሙስና ህግ መጥቀሱ በቂ ነው ሌላው ቫትን በተመለከተ የወጣው አዋጅ ነው ይህ አዋጅ መጀመጀሪያ ሲወጣ ያማከለው ገቢያቸው ክ500000 በላይ ለሆኑና አላማውም እነዚህ ነጋዴዎች ገቢያችው ከአነስተኞችሁ ስለሚሻልና ተገልጋዮችም ገቢያችው ደህና ስለሆነ ከእነሱ ላይ በቀጥታ ተጭማሪ ግብር በሚጠቀሙበት ላይ ለማግኘት ነበር ግን ነገሩ የጣመው ወያኔ ሁሉም ላይ ክንዱን አሳረፈው ከዚያ አንድ አባውራ ለህጻን ልጁ ወተት ከሱፐር ማርኬት(የላም ወተትማ ህልም ነው )ለመግዛት ሲሄድ ከወር በፊት ከነበረው አስር እጥፍ ዋጋ ጨምሮ ጠበቀው ምክኒያት ያው ውተቱ ከተመረተበት ቦታ ጀምሮ ገዚው ጋር እስከሚደርስ አራት ግዜ ተቀርጦ ስለሚመጣ ነው ከዚያ አሁን ለምናየው የኑሮ ምስቅልቅል ላይ ደረስን ነጋዴው እንደፈለገ ይሸጣል ይገዛል ሲያሻው ጥሬ ዕቃ ይደብቅና ግዜ ጠብቆ በፊት ከነበረው አስር እጥፍ ዋጋ ጨምሮ ይቸበችባል ፣ዋጋ ተማኝ ነጋዴው ራሱ የተመነውን ዋጋ አስተካካይ ራሱ ሆኖ አረፈው።

ለዚህ አስረጅ የሚሆነው በአንድ ወቅት ጨው ሊጠፋ ነው ተብሎ የጨው ዋጋ የት እንደደረሰ የሚታወስ ነው፣ ይሄ ነው እንግዲህ የህገ አራዊትና የሰው ህግ ልዩነት አራዊቶች እንደፈለጉ ይኖራሉ ወደፈለጉት ይሄዳሉ ጡንቻቸው ሲፈረጥም የፈለጉትን ገለው አካባቢውን የራሳችው አድርገው በማናለብኝነት ይኖራሉ የወያኔም ባህሪ ይሄ ከሆነ ሰንብቷል ለነገሩ ይሄ ባህሪ ጫካ እያሉ የተጠናወታቸው ሰለሆነ የሚለቀውም ሆነ የሚጠፋው መዝገር የሆኑብንን ጠላቶች ከላያችን ላይ ስናራግፋችው ብቻ ነው ።

ይሄ በለውጥም ሆነ በሰው ልጅ የሰባዓዊ መብት ላይ የማያምንንና የማያከብር ቡድን አንዴ ከጭንቅላታችን ገማን እያሉ ለገማው ነገራቸው አንድንም ቀን መፍትሄ ሳይፈልጉ ዛሬ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብለው የተቀመጡት ሰውየ አገር የምመራው በግምት ነው በለውን አረፉት ጉድ ያለው ገንፎ ……..፣ አንዳንድ አስተያየት ሰጭወች እንደሚሉት ከሆን መንግስት በድንገት እንዲህ ያለ ረብሻ ውስጥ የገባው በሁለት ነገሮች ነው

1ኛ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ እጥረትና የአበዳሪዎች መጥፋት

2ኛ አገሪቷ ውስጥ ያለው የገንዘብ የመግዛት አቅም ማነስና መንግስት በተለይ ለስለላና ለወታደሩ የሚያወጣው ገንዘብ እንዳይቀንስና ከሚተማመንበት ቦታ ሃይል እንድይከዳው ህዝቡን በተለያዩ የገቢ ማግኛ ዘዴ በማስገደድ ካለበት አጣብቂኝ መውጣትና የስልጣን ግዜውን ማራዘም፣ ይሄ እንግዲህ ለጠቅላዩ አይነገራችውም ብቻ እሳችው በውሸታሙ ቲቭ መስኮት ብቅ ይሉና ተቀዣብረው ያቅባዠራሉ ። ለሰሞኑ የጠቅላያችን ሁናቴ የምትስማማ ግጥም ልጋብዛቸውና ጹፊን ልቋጭ።

ለቀዶ ጥገና
እንመጣለን ገና
ቀዳጁ በዛና
ተቀደን ተቀደን ተቀደን አለቅና
ቀዳጁ ቀዳጁ
ብሷል በወዳጁ ።
እንዴነሽ እንዴነሽ ዶፍተርየ እንዴነሽ
ላላጣሽው ሙያ ቀደዳ ተምረሽ
ቀደሽኝ ቀደሽኝ ቀዳደሽኝ ቀረሽ
ኧረ ያንቺስ ነገር ለወሬም ይከብዳል
መስፊያው ሳይዘጋጅ እንዴት ይቀደዳል ?
ዘወር አርገው ጋሜ
አይዞህ ወንድሜ
ቀድሞም ተዟዙረህ ተፈጥረሀልና
አዙረህ አዙረህ አዟዙረኸውና
ተብለሀልና
መልሰህ ለማዞር ድከም እንደገና

እንቅልፍና ዝለት ምን ቢመሳሰሉ
በውግና በወግ ደንዝዟል እያሉ
አንዴት ይቀደዳል ያሸለበው ሁሉ ?
መለስ አርገው ጋሜ
አይዞህ ወንድሜ
መልሰው መልሰው መልሰህ መላልሰው
እንዲያ ሲሆንጅ “እንዲያው ሰው” አይሆን ሰው ።
በዘመነ ራዕይ
ዘመናይት አድባር ክፉ ልማድ ለምዳ
ከሰብአዊ ጅረት ደም እየተቀዳ
ቀዶ ቀዶ ቀዶ
ቅዱ ሳይሰፋ መልሶ ቀደዳ
መልሶ መልሶ መላልሶ ቀደዳ
ቀደዳ
ቀዳዳ
ቀደዳ

LEAVE A REPLY