የሳኡዲ የምህረት አዋጁ አለመራዘሙን የሃገሪቱ ጋዜጦች አስታወቁ

የሳኡዲ የምህረት አዋጁ አለመራዘሙን የሃገሪቱ ጋዜጦች አስታወቁ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦  የሳኡዲ የምህረት አዋጁ አለመራዘሙን የሃገሪቱ ጋዜጦች አስታወቁ
በጅዳ የሚገኘው የኢትዬጲያ ቆንጽል ጽ/ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ “የምህረት አዋጁ” ከሐምሌ 17/200ዓ.ም ጀምሮ በድጋሚ ለአንድ ወር መራዘሙን ገልፆ ነበር።

ይሁን እንጂ በሳኡዲ አረብያ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚታተመው ሳኡዲ ጋዜጥ ( saudigazett) የጀዋዛትን ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ሱሌይማን አል ያህያን አነጋግሮ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የሳኡዲ የምህረት አዋጅ አለመራዘሙን አስታውቋል።

በመሆኑም የኢትዬጲያ ኤምባሲ የጅዳ ቆንስል ቢሮ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱ ዜጎችን ለእንግልትና ለችግር የሚዳርግ ነው።አሁንም የኢትዬጲያ ኤምባሲ በሳኡዲ አረብያ ሪያድ እና ጅዳ ቢሮ ለዜጎቹ የተረጋገጠና የተጣራ መረጃ በአስቸኳይ ለዜጎቹ የማሳወቅ ግዴታ ያለበት በመሆኑ ይህንኑ ያደርግ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መረጃውን ያወጣውን ጋዜጣ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡት።

http://saudigazette.com.sa/article/513869/

SAUDI-ARABIA/Amnesty

LEAVE A REPLY