አርቲስት ተስፋየ ሳህሉ(አባባ ተስፋየ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አርቲስት ተስፋየ ሳህሉ(አባባ ተስፋየ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦  በኢትዮጵያ ራድዮና ቴሌቪዥን ለልጆች ተረት ሲያቀርቡ የምናውቃቸው አባባ ተስፋየ (ተስፋየ ሳህሉ) በተወለዱ በ94 ዓመታቸው ከዚህ አለም ዛሬ በሞት ተለይተዋል። አባባ ተስፋ የበርካታ ሙያ ባለቤት ነበሩ።የተረት አባት፣የመድረክ መሪ፣ቲያትረኛ፣የዜማና ግጥም ደራሲ፣የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ድምጻዊ ወ.ዘ.ተ ሲሆኑ በተሳተፉበት የሙያ መስክ ሁሉ ስኬታማና ተወዳጅ ነበሩ።

“ጤና ይስጥልኝ ልጆች! የዛሬ አባባዎች የነገ ፍሬዎች፤ እንደምን አላችሁ ልጆች!› በሚል አባታዊ ለዛ ታጅበው ከ50 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ራድዮ እየቀረቡ ተረት በማውራት ህፃናት ልጆችን ሲያንፁ የኖሩ ታላቅ የሞራል መምህር ነበሩ።

አባባ ተስፋየ ከ1937 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ለ8 ዓመታት፤በኢትዮጵያ ቲያትር ቤት ደግሞ ከ50 ዓመታት በላይ የተለያዩ ቲያትሮችን በመስራት ለኪነ-ጥበቡ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አበርክተዋል።

በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ይሰሩ በነበሩበት ወቅት የሴት ተዋናይት ባለመኖሩ፤እርሳቸው የሴት ገጸ-ባህሪያትን ጭምር በመላበስ ተጫውተዋል።ከእነዚህም ጎንደሬው ገብረማርያም፣ጠላ ሻጭ፣ቴዎድሮስ፣መቀነቷን ትፍታ የሚሉት ቲያትሮች ይጠቀሳሉ።

አርቲስት ተስፋየ ሳህሉ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሚያቀርቡት የልጆች ተረት ከፍተኛ ተወዳጅነትን ቢያተርፉም በ“ውሀ ቀጠነ”ምክንያት ለጆችን በመልካም ስነ-ምግባር እንዳያንጹ “በስርዓቱ” ተከልክለው ለዓመታት ከሙያቸው ተለይተው ቆይተዋል።

አባባ ተስፋየ ከሚታወቁባቸው ንግግሮቻው መካከል፤

“ ጤና ይስጥልኝ ልጆች! … የዛሬ አበባዎች፤ የነገ ፍሬዎች! … እንደምን አላችሁ ልጆች! … አያችሁ ልጆች! … የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ዝግጅት እናንተን ለማስደሰት ልክ በሰዓቱ ይገኛል።

አባባ ደሞ የልጆች ሰዓት እንዳያልፍባቸው በሩጫ ዲ ዲ ዲ ከተፍ ፤ እናንተ ደግሞ ቆማችኃል። ይሄ በጣም ጥሩ ነው ልጆች። አንድ አባት ሲመጣ በአክብሮት መነሳት አስፈላጊ ነው …………።”

LEAVE A REPLY