በጎንደር የእስር ዘመቻ ተጀመረ

በጎንደር የእስር ዘመቻ ተጀመረ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በጎንደር ከተማ አዲስ የእስር ዘመቻ መጀመሩ ታወቀ፡፡ ከስፍራው የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት ከነሐሴ 10 እስከ 15/2009 ዓ.ም የተጠራውን የስራ ማቆም አድማ ያስተባብራሉ ተብለው የተጠረጠሩት የከተማዋ ወጣቶች በገፍ እየታሰሩ መሆኑን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። “ተቃውሞ ለማስነሳት፣ አድማ ለመጥራትና ሽብር ለመፍጠር ተንቀሳቅሳችኋል” የሚል ውንጀላ እንደቀረበባቸውም ታውቋል።

የከተማዋ ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጥ “በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ብጥብጥና የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሶስት የባጃጅ አሽከርካሪዎችና በመድኃኒዓለም ክፍለ ከተማ ደግሞ ለአድማ የሚያነሳሳ መልዕክት የያዘ ወረቀት ሲበትኑ የነበሩ አምስት የፀረ ሠላም ኃይሎች ተላላኪዎች ተይዘዋል”” ብሏል፡፡ ፖሊስ አክሎ እንደገለጸው ከስምንቱ ወጣቶች በተጨማሪም በከተማዋ የቦንብ ጥቃት ሊያደርሱ ነበር የተባሉ ሌሎች ሁለት ወጣቶችም ታስረዋል፡፡ ፖሊስ 10 ወጣቶችን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ቢገልጽም የታሰሩት ወጣቶች ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል።ምርመራ እየተደረገባቸው እንሆነም ታውቋል፡፡

ሰላም ከራቃት ከዓመት በላይ በሆናት “በጎንደር ከተማ” የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አዳርጓቸው “ከፍትህ፣ ከፖሊስና ከባለ ድርሻ አካላት” ጋር ከሰኞ ጀምሮ ስብሰባ ተቀምጧል።ተሰባሳቢዎቹ ባልተለመደ ሁኔታ በድፍረት የተለያዩ ጥያቄዎች ለአቶ ገዱ መቅረባቸው ታውቋል።ከጥያቄዎቹ መካከልም የወልቃይት ጉዳይ፣በክልሉ በውሸት ውንጀላ ስለሚታሰሩ ሰዎች፣ጎንደርን ከሦስት ለመክፈል የታሰበው ከጀርባው ተኮል አለው፤በመሰረተ-ልማት ወደ ሗላ መቅረትና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች በስፋት መነሳታቸውን ምንጮች ጠቅሰዋል።ስብሰባው እስከ አርብ እንደሚቀጥልም ታውቋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞ ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የህወሓት ቡድን፣ ሰበብ እየፈጠረ ሰዎችን ማሰሩን ቀጥሎበታል፡፡ የእስር ዘመቻው በጎንደር፣ባህር ዳር፣ደብረታ ቦር፣ወልድያ፣ኮምቦልቻና በሌሎች ከተሞችም ተጠናክሮ ቀጥሏል።
አሁን ባለን መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ ከ500 በላይ ነጋዴዎች መታሰራቸውንና “የፈጠራ ክስ” እየተመሰረተባቸው መሆኑ ታውቋል።ከተመዋ በመከላከያ ሰራዊት መወረሯና የታሸጉ ሱቆች እስካሁን እንደተዘጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY