የአውሮፓ ህብረት የኬንያ የምርጫ ውጤት በኦንላይን እንዲለቀቅ ጠየቀ

የአውሮፓ ህብረት የኬንያ የምርጫ ውጤት በኦንላይን እንዲለቀቅ ጠየቀ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን በኬንያ ነሐሴ 8/2017 የተደረገውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በወረቀት የሰፈሩ ቅጾችና የድምጽ ውጤቶች በድህረ-ገጽ በመልቀቅ ፤የምርጫውን ግልጽነትና ትክክለኛነት ማሳየት እንዲቻል ለኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ቃል አቀባይ የሆኑት አንድሪው ሊሞ እንዳሉት ከ41000 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 2900 የሚሆኑት በድህረ-ገጽ ይፋ መደረጋቸው መልካም ነው ካሉ በሗላ የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ሁሉንም የመራጮች ድምጽ የያዘ ሰነድ ይፋ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

ምርጫውን ከታዘቡት አለም አቀፍ ተቋማት መካከል የአውሮፓ ህብረት አንዱ ሲሆን በወቅቱ የሰጠው መግለጫም “ምርጫው ነፃና ፍትሀዊ” ነው ማለቱ ይታወሳል።

በምርጫው ፕሬዚዳንት ሁሩ ኬንያታ በ54.3 ፐርሰንት ዳግም ማሸነፋቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ ቢያደርግም 44.7 ፐርሰንት ድምጽ አግኝተዋል የተባሉት ተቀናቃኙ ራይላ ኦዲንጋ ውጤቱን አልቀበልም ብለዋል።ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት ወስደው እንደሚሞግቱም አስታውቀዋል።

በድህረ ምርጫው በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍል “ምርጫው ተጭበርብሯል” በሚሉ ወገኖች ግጭት ተፈጥሮ የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

የተቃዋሚዎች ጥምረት የሆነው “ናሽናል አሊያንስ” ከ100 በላይ ሰዎች በፖሊስ ጥይት መገደላቸውን ሲገልጽ መንግስት በበኩሉ 11 ሰዎች መሞታቸውን አምኗል።ሚዲያዎችና ገለልተኛ ተቋማት ደግሞ የሞቱት ሰዎች 24 ናቸው ብለዋል።

በዚህ ምርጫ ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሁሩ ኬንያታ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት መሰረት ከሁለት ዙር በላይ ሀገር መምራት ስለማይችሉ፤ ራይላ ኦዲንጋ ደግሞ በእድሜ ገደብ ዳግም ለውድድር አይቀርቡም።

LEAVE A REPLY