ባላራዕዩ መሪያቸው ሲታሰቡ! /ኢሳት-የሃሳብ መንገድ/

ባላራዕዩ መሪያቸው ሲታሰቡ! /ኢሳት-የሃሳብ መንገድ/

የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ይህቺን ዓለም ከተሰናበቱ አምስት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ሀገሪቱን በሙት መንፈስ የሚያምሱት ገዢዎችና ተከታዮቻቸው ደጋግመው እያነሷቸው ይገኛሉ። ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ የተረፈ ራዕይ የነበራቸውና ዓለምንም ያጎደሉ ስለመሆናቸው አብዝተው እየተናገሩላቸው ቢሆንም፣ ጥላቻ ያመቀና ዘረኝነትን በልቡ የሰነቀ እንዴት ሀገራዊ እንደምንስ አህጉራዊ ራዕይ ይኖረዋል? በመንደሩ ፍቅር የወደቀና ጽልመትን አውርሶን፣ በተግባር የዓለም ግርጌ አድርጎን የሄደ፣ እንደምንስ ሃገራዊ ሕልም ይኖረዋል ብሎ መጠየቁ፣ ከሙት ጋር ሙግት መግጠም ሳይሆን፣ በሙት መንፈስ ሀገሪቱን ለሚያምሱ መልዕክት ይሆናል።

LEAVE A REPLY