በጅማ ከተማ በቦምብ ጥቃት 13 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

በጅማ ከተማ በቦምብ ጥቃት 13 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በጅማ ከተማ እኩለ ቀን አካባቢ በተጣለ የእጅ ቦንብ በ13 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል። ቦንቡ የተጣለው ለገሃር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦችም በጅማ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ህዝባዊ እቢተኝነት ከተጀመረ ከሁለት ዓመታት ወዲህ መንግስት በየቦታው ቦንብ በማፈንዳት በህዝብ ለማመካኘት ሲሞክር መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬም በጅማ የፈነዳው ቦንብ የዚሁ አካል ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። ትናንት የተጀመረው ከቤት ያለመውጣት አድማ ዛሬም በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ አወዳይና ሀረማያ በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ፣ኮፈሌ፣አዳባና አሳሳ በምዕራብ ሸዋ አምቦና ጊንጪ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነቀምቴ፣ጊምቢና ነጆ በአዲስ አበባ ዙሪያ ቡራዩ ከተማ ሱቆችና ባንኮች ዝግ ሆነው ውለዋል።

LEAVE A REPLY