የሳዉዲ አረቢያ መንግስት 450 ሽህ ኢትዮጵያንን በሀይል ለማስወጣት ማቀዱን አስታወቀ

የሳዉዲ አረቢያ መንግስት 450 ሽህ ኢትዮጵያንን በሀይል ለማስወጣት ማቀዱን አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦  የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን 450 ሽህ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በሀይል ከሀገሩ ለማስወጣት እቅድ ማውጣቱን አስታወቀ። እስካሁን 160 ሽህ ኢትዮጵያዊያን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱም ታውቋል።አብዛኛዎቹም በየእታሰሩበት ካምፖች ውስጥ ተለቅመው ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በሗላ በመንግስት የማሰቃየት ተግባር እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ሂዩማን ራይትስ ዎች አስታውቋል።

ሳውዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ካስታወቀች ካለፈው መጋቢት ወር ጀምሮ 45000 ኢትዮጵያዊያን ብቻ በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልጸዋል። ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የምህረት አዋጁ ነሐሴ 17/2009 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወቃል።

ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሀገራቸው የማይመለሱበት በርካታ ምክንያቶች ቢኖሯቸውም፤ ዋነኛው ግን በመንግስተቸው የሚደርስባቸውን የተለያዩ በደሎች በመፍራት ነው ተብሏል። ሳውዲ አረቢያ የስደተኛ ህግ የላትም። የተባበሩት መንግስታትም የስደተኞች “የስምምነት” ህግ አካል አለመሆኗን ዛሬ ሚድል ኢስት ሚረር ዘግቧል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች ሐሙስ እለት ባወጣው መግለጫው ከግማሽ ሚሊየን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሀገሯ በሃይል እንዳታባርር ሳውዲ አረቢያን መጠየቁ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY