“በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም ችግሩ እንቀጠለ ነው” አፍሪካ ኮንፊዴንሽያል

“በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳም ችግሩ እንቀጠለ ነው” አፍሪካ ኮንፊዴንሽያል

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ በኢትዮጵያ የገዥው ፓርቲ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ፓርላማ ለአስር ወራት ጥሎት የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካነሳው አንድ ወር ቢሆነውም በሀገሪቱ ውስጥ ቀድሞ የነበሩት መሰረታዊ ችግሮች አሁንም እንዳሉ ነው ሲል አፍሪካ ኮንፊዴንሽያል የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ይፋ አደረገ።

ሀገሪቱን የሚመራት የኢህአዴግ መንግስት ያለውን ቀሪ እድል ከመጠቀም ይልቅ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ ወረቀት ላይ ብቻ በማስቀመጥ እድሉን እያባከነ ነውም ብሏል። ስርዓቱ አመራር በመቀየር እንዲሁም በሙስና ጠረጠርኳቸው ያላቸውን ከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባል ቢያስርም በህዝቡ ዘንድ እምብዛም ትኩረት አላገኘም በማለት ድርጅቱ ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ለዓመታት የዘለቀው የህዝብ ትግል ከቀን ወደ ቀን አድማሱን እያሰፋ የመጣ ሲሆን የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄም የማንነት፣የእምነት፣ፍትሀዊ የሀብት ተጠቃሚነት፣የዲሞክራሲና የስርዓት ለውጥ በስፋት መነሳቱ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY