የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ ውድቅ አደረገ

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ ውድቅ አደረገ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነሐሴ 8/2017 የተካሄደውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድቅ በማድረግ በሁለት ወር ውስጥ እንደገና እንዲካሄድ ዛሬ ውስኔ አሳልፏል፡፡

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሁሩ ኬንያታን በ54.3 ፐርሰንት የምርጫው አሸናፊ መሆናቸውን ማወጁ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ተፎካካሪያቸው ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ቆጠራ የተካሄደባቸው ኮምፒተሮች ተጠልፈው ውጤቱ በመዛባቱ አልቀበልም በማለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫ ኮሚሽኑን፣ የፕሬዚዳን ሁሩ ኬንያታንና የራይላ ኦዲንጋን ክርክር ካደመጠ በሗላ ምርጫው የሀገሪቱን ህገ-መንግሰት የተከተለ አልነበረም በማለት በ60 ቀናት ውስጥ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ወስኗል።

ከሳሽ ራይላ ኦዲንጋ በፍ/ቤቱ ውሳኔ መርካታቸውን ገልጸው፤ የምርጫ አስፈጻሚው አካል አንዲቀየርና በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል። ደጋፊዎቻቸውም በመላ ሀገሪቱ ደስታቸውን እየገለጹ ነው። በሌላ በኩል ሁሩ ኬንያታ በግላቸው በፍ/ቤቱ ውስኔ አልስማማም ነገር ግን እቀበላለሁ፤ አከብራለሁም በማለት ገልጸዋል።

በኬንያ የሚገኙት የአሜሪካና የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደሮች የኬንያ ፍ/ቤት ለአፍሪካ ምሳሌ ነው፤ ኬንያዊያንም በህግ ስርዓታቸው ያላቸውን እምነት አድንቀዋል።

LEAVE A REPLY