የፋሽሽቱ ወያኔ ጎንደርን የመከፋፈል አደገኛ ዘመቻ ኢትዮጵያን የማፈራረስ የመጨረሻው ደወል ነው (የጎንደር...

የፋሽሽቱ ወያኔ ጎንደርን የመከፋፈል አደገኛ ዘመቻ ኢትዮጵያን የማፈራረስ የመጨረሻው ደወል ነው (የጎንደር ሕብረት)

ይድረስ ለጎንደር ህዝብ (ቁጥር 13)

ባለፉት ሶስት አመታት በተደጋጋሚ እንዳሳሰብነዉ የጎንደር ህዝብ በአንድነት ቆሞ በዉስጥም በዉጭም ያለዉ ኢትዮጵዮያዊ ሁሉ ተባብሮ የጠላትን ሴራ ለማክሸፍ ብቃት እንዳለዉ በሙሉ ልብ አስገንዝበን ነበር። አሁንም የዛሬዉ ጽሁፋችን የሚያተኩረዉ ወያኔ መልሶ መላልሶ የሚያመጣዉን የመከፋፈል አጀንዳ አደገኛነቱን ለማሳሰብ ነዉ።

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር አዲስ አበባ ከገባ ጀምሮ አገራዊ ታሪክን የማበላሸት አባዜ የተጠናወተዉ በድርጊት ለመተግበር ያልቆፈረዉ ጉድጓድ የለም። ዳር ድንበር ቆርሶ አገር አፍርሶ የታላቋን ትጋራይ የበላይነት ለዘመናት እዉን የማድረግ ዘመቻ ህዝባችን በትግስትና አስተዋይነት የተጸነሰዉን ሤራ በኢትዮጵያዊያን ጸንቶ የኖረ ትብብር እየተመታ አብዛኛዉን ህዝብ አክሽፎታል።

በርግጥም በታሪኩና በደሙ አንድ የሆነዉ ህዝባችን ተባብሮ እያካሄደ ያለዉ የአመጽ የትግል ማዕበል የወያኔን የስልጣን መንደርተኞች እያሽበረ መሆኑን ስናይ እጅግ የሚያኮራ ነዉ። ፋሽሽቱ ftድን ፍጹም ከማይወጣዉ አረንቋ መዘፈቁንም በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። የህዝባችን ትብብር እና ታሪካዊ ጀግንነቱ ከምንጊዜዉም በበለጠ ገሃድ እየሆነ ፤ወያኔን እያርበደበደ የሴረኛዉን እቅድ ሁሉ አሟጦ እንዳቧራ አጭሶታል ። በአሁኑ ሰዓት በብልጣብልጥነት የተገነባው ትቢት ተንዶ የህዝብ ድጋፍ ጭራሽ አቶ እቅዱ ሁሉ የማይጨበጥ ንፋስ ሁኖ የዉሸትና የዉድቀት ዲስኩር እየደሰኮረ እርቃኑን ቁሞ ይገኛል።

ገና ከፅንስሱ የዘረኛነት በሽታ የተጠናወተዉ ወያኔ የጎንደርን ህዝብ አብሮነት እና ታሪካዊ አንድነት ለመሸርሸር፣ ተከባብሮና ተፋቅሮ የሚኖር ህዝብን አለያይቶ ለማጋጨት ተሰማርቶ ጎንደር ላይ የዘረኝነት ማካለል በተደጋጋሚ ቢከሽፍም አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ሴራዉን ለማሳካት ትልቅ ዘመቻ ከፍቷል። ይህንንም የወያኔ እኩይ እንቅስቃሴ ህዝባችን በአንድ ላይ አብሮ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በተባበረ ህዝባዊ ሃይል መታት አለበት ።

የብሄሮች ድሞክራሲ ጭምብል ለብሶ አናሳ ጎሳወችን ልጠቅም ነኝ በሚል ፈሊጥ አንቀጽ 39 በመተግበር 26 ዓመታት ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመዉን ስልት ዛሬም ጣረሞት ላይ እያለ ቅማትና አማራን በመንደር ከልሎ የማይጠፋ ጠባሳ ለመፍጠር በምርጫ ቦርድና በካድሬወቹ አማካኝነት በቴሌቢዥን መስኮት ብቅ ብሎ የመርዝ አዋጁን በመርጨት ላይ ይገኛል።

ለጎሳወች/ለነገዶች ከእዉነት አሳቢ ቢሆን ኑሮ በትግራ ዉስጥ የራሳቸ ዉ ቋንቋና ባህል ያላቸዉ ለዘመናት የኖሩ ማህበረሰብ አሉ፤ ለምሳሌ ሳሆ፤ ብሌን፤ ፤ ኩናማ ፤አገዉ ፤ አፋር፤ኢሮብ ቤጃ ሌሎችም መዘርዘር ይቻላል፤ ነገር ግን በወያኔ ጨዋታ የጧት ማታ ቀረርቶ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ዘይቤ አንድም ቀን በትግራi ዉስጥ የሚኖሩትን ስማቸዉን አንስቶ አያዉቅም።

ሃቁ ግን አሁንም የጥንቱ ትግራይ ክፍለ ሀገር አንድነቱን ጠብቆ ተባብሮ እየሰራ የጫካ ደንን በማሳደግ፤ የትባኮ አጫሽን በማስወገድ በስልጣኔ እድገት ትግራይ እንደ አገር ተወዳዳሪ ሁና በዓለም መድረክ ወርቅ ተሸላሚ ሆነች እዬተሰማነዉ። እንዲዉም አገርና ህዝብን የሚንቀዉ ወያኔ የጎንደርን ደን እና ጫካ በትግራይ ስም አስተዋዉቆ መሸለሙን የሚያረጋግጥ የራሱ ልሳን በሆነዉ የዜና አዉታር (በኢቢሲ) ከጎንደር እስከ ጋምቤላ ለታላቋ ትግራይ ያለመዉን ካርታ አሳይቷል። ከዚህ የበለጠ በዓለም ደረጃ አይኑን አፍጦ የመጣ ሃገራዊ አደጋ የለም ። ለምን ይህ ሆነ? የሌላዉን ክፍለ ሃገራትን ወያኔ እየሸነሸነ የትግራይን አንድነት አስከብሮ የቀጠለዉ ለምን ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ለመመለስ ሊቅ መሆንን አያስፈልግም።

በታሪካዊቷ የጎንደር ክፍለ ሃገር የሚኖር ማህበረሰብም ኢትዮጵያዊ ሁሉ አማራዉ፤ ቅማንቱ፤ ሽናሻዉ፤ ቤተ እሥራኤሉ፤ ጉምዙ፤አገዉ ተባብሮ በአንድነት የቤጃ ምድር (ቤጌምድር) ያልተከፋፈለች ጠንካራ የጎንደር ክ/ሐገር የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር ሆና እንድትዘልቅ ከመቸውም የበለጠ ተባብረን በድል ለመወጣት ታሪካዊ አደራ ተጥሎብናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! አንገብጋቢዉ ጥያቄ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት በኢፈርት አማካኝነት መዝረፉ፣ በአንድ ጎሳ የበላይነት ወያኔ ኢትዮጵያን እያጠፋ የመሆኑ የነጻነት ጩኸት ጀሮ ዳባ ልበስ በሚል ታዳፍኖ ፣ በዜግነት መኖር ጭራሽ ጠፍቶ፤ ፍትህ ተጓሎ፤ ዳር ድንበር ለብአድ አገር ተሽጦ፣ ዜጎች በመቶ ሽወች እስር ቤት እየማቀቁ ባሉበት አሰቃቂ ሁኔታ ለቅማንት ማህበረሰብ ተቆርቁሪ መስለው፣ በአስቸኳ የማካለል ዉሳኔ እሰጣለሁ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ሆድ ሲያዉቅ ደሮ ማታ ነዉ።

የጎንደር ህዝብ ብሎም የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ እዬሞተ ባለዉ የወያኔ የዉንብድና ዘረኛ ስርዓት ከእንግዲህ አይጃጃልም። በዜረኝነት ተወልዶ በመከፋፈል በሽታ የሚሞተዉ ወያኔ አሁንም እንደትናንቱ ጎንደር ላይ እሳት ለመለኮስ ኮሮጆ እና ክብሪት አሸክሞ በካድሬወቹ አማካኝነት ለመተግበር እየጠነሰሰ ያለዉን ሴራ ህዝባችን ዉርደትን አከናንቦ ለመመለስ ከዳር እስከዳር መነሳት አለበት።

የጎንደር ሽንፈት ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የወያኔ የባርነት አፋኝ ሥርዓት ቀጣይነት በመሆኑ ህብረታችን የሚከፋፍሉ አክራሪወችን ጥፉ ብለን ወያኔን በአስቸኳይ አስወግደን ሁሉም ኢትዮጵያያን በነጻነት በፍትህ/በህግ የበላይነት በእኩልነት ህዝባዊ መንግስት መስርተን ለመኖር መዘጋጀት አለብን። ከዚህ የተሻለ ሌላ ምርጫ የለንም።

በሚሊዮን ብር ባጀት የሚንቀሳቀሱ ባንዳ ካድሬወች ቅስማቸዉ እንደገና ሊሰበር ይገባል።

በመሬት ስርቆት የሰከረዉ ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የወሎ ራያን መሬት ወደ ጥንት አስተዳደር የመለስልን ጥያቄ ዉድቅ አድርጎ በአንድነት ምሰሶ ጸንቶ የቆመዉን የአማራና ቅማንት ማህበረሰብ እርስ በእስ ለማናከስ የቅማንት ክልል ለመፍጠር በቅርብ ጊዜ የሕዝብ ጥያቄና ፍላጎት ያለ በማስመሰል የለመደውን የማጭበርበሪያ የድምፅ ኮሮጆ ይዞ ወደ ጎንደር ብቅ ማለት ትልቅ ድፍረት ነውና ይህ መሰሪና ዕኩይ የወያኔ ተልዕኮ በሕዝባችን አንድነት ሊገታ ይገባዋል።

እነ ኮኔሬል ደመቀ እና የኮሚቴ አባላት አሥራ አንድ ጊዜ አዲስ አበባ በመመላሳቸዉ ብቻ ምንም ወንጀል ሳይሰሩ ታፍነዉ ተወስደዉ ባሁኑ ሰዓት በእስር እየማቀቁ ነዉ። አርበኛ ጀግኖች እነ ጎቤ መልኬ፤ ሰጠኝ ባብል ፤ሢሳይ ታከለ እና ብዙ ጀግኖች መስዋትነት የከፈሉበት ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ ቅማንትና አማራን ለመከፋፈል ህዝበ ዉሳኔ እሰጣለሁ ብሎ ሳይጠሩት ወያኔ አቤት ማለቱ ቀቢጠተስፋ የሆነ የታሪካዊ አጥፊ ጠላቶች የማያቋርጥ ቅሌት መሆኑ ግልጽ ነዉ። በተጨማሪም ይህ ዘመቻ ጎንደርን በትኖ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሱዳን ጋር የጠነሰሰ ሴራ መሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዉቀው  እንፈልጋለን።

በመቶ% ተመርጫለሁ ብሎ የዓለም ሁሉ መሳቂያ የሆነዉ ወያኔ ካሁን በፊት በኮሶዬ፤ በድባ አቦ፤ በጭጋሳ፤ ለማጭበርበር በሚስጥራዊ ወረቀት ምረጡ ብሎ ዘምቶ ተዋርዶ ተመልሷል። አሁንም ጎንደር ዉስጥ ቅማንትና አማራን ለማካለል የየሚደረግ እርምጃ በቦንብ ላይ መቆም እንደሆነ እንዲታወቅ ግድ ይላል።

ህዝft መከፋፈልን አንሻም ብሎ የተቃወመዉን ሕዝባዊ አቋም ወያኔ ከቁም ነገር ሳይቆጥር፤ አብዛኛዉን የክልል ተወካዮችን ተቃዉሞ ድምጽ ቀልብሶ በማስፈራራት የሃይል የበላይነቱን ለማሳየት በፌደራል ስም ጎንደርን ለመከፋፈል የሚያካሂደዉ ዘመቻ የመጨረሻ የስራቱ መቃብር ሊሆን እንደሚችል እና እራሱን በራሱ ለማጥፋት እያፋጠነ መሆኑን እንደገና የሞት መርዶ እርሙን እንዲያወጣ በጥብቅ እናሳስባለን።

የጎንደርን ሕዝብ ታሪካዊ አንድነት ጠምዝዞ በጉልበት ለማንበርከክ የሚፈጸም ተደጋጋሚ ሥልጣንን ተገን ያደረገ የጥፋት ዘመቻ ለትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የሞት ከፈን ከመሆን ሌላ የጥፋት ሴራዉን ሊያሳካ አይችልም።

የፋሽሽቱ ftድን የማካለል ዋነኛ እስትራቴጂ የአንጡራ ሃብት ለመዝረፍ ለያይቶ ደካማ መንደር ለመፍጠር ነዉ። ከብዙ በትንሹ ምሳሌ ለመጥቀስ የአዊ ዞን ፤ የቢሻንጉል፤ የጋምቤላ ዞን ፈጥሮ ህዝftን ከቅድመ አያቱ እርሻ እያፈናቀለ መሬቱን ለካድሬወችና ለጀኔራሎች የዘረፋ ምንጭ አድርጎታል። በኦሮሞና በሱማሊያ በደftብ ህዝቦች የሚካሄደዉ ዘረፋ እና ግጭት ከልክ ያለፈ መሆኑ በዬቀኑ እዬታዬ ያለ ተጨባጭ ሃቅ ነዉ።

አሁን ቅማንትና አማራን ለማካለል ወያኔ አይኑን ጨፍኖ የተነሳበት ጉዳይ የሁመራ ፤የቃብትያ የጠገዴ ጠለምት ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጄል ፈጽሞ መሬቱን ለአርባ አመታት ነግሶ ቆይቷል። አሁንም የቀሩትን የጎንደር ለምና እዉኃ ቀመስ መሬቶች ለታላቋ ትግራይ ቋሚ ንብረት እንዲሆኑ የግድ የተጨቆነ ቅማንት በሚል አጥር ሸብቦ/አጉራ ዉስጥ አስገብቶ መቀየድና በካርታ ያስቀመጣቸዉን ከመተማ እስከ ጋሚቤላ በሱዳን ትብብር የጋራ መሬት ተካፋይ ለመሆን ሰፊ እቅድ በመያዙ ነዉ።

ይህ እቅድ ደጋግመን የገለጽነዉ እና የወያኔ የመጨረሻ ግብ ነዉ። ይህ ሴራ ለጎንደር ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ ቀጣይ ሉአላዊነት አደገኛ መርዝ ነው። ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ይገደናል የምንል ሁሉ በአንድ ላይ ተባብረን የማክሸፍም ሆነ ይንህን ከአፋፋይ ስርዓት የማስወገድ ሃላፊነት ታሪክ ጥሎብናል።

ጉዳዩ በሁለት ጠላት አፈሙዝ እዬተወጋን ነዉ። ከሱዳን ጋር ለምና ዉሃ ቀመስ መረትየመጋራትን አላማ ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ቋራ ነብስ ገቢያ ከተባለዉ የጎንደር/ኢትዮጵያ መሬት ዉስጥ አንድ የሱዳን ክፍለጦር አስቀምጧል፤ ይህ የዉጭ ተደራቢ የጠላት ሰራዊት የጋራ ጸጥታን ለማስከበር በሚል ለአለፉት ሁት ዓመት ወያኔ የሰጠዉን መረት በማቋቋም ላይ ይገኛል።ለአስር ዓመት የጎንደርን መሬትን አዋሰ የሚለዉ ዜና ወያኔ በትግራይ ባለቤትንት ስም የተፈረመ እስከመጨረሻዉ የተሰጠ መሬት ነዉ። ይህም ከሱዳን ጋር ጎንደርን የመሸንሸን እንቅስቃሴ የወደፊቱን የቋራን የምራብ አርማጭሆን መተማን ጨምሮ ከቢሻንጉልና ጋምቤላ አገናኝተዉ በታላቋ ትግራይ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ሥር ለማዋቀር የታሰበ ነዉ። አደጋዉ ይህን ያህል የከፋ ነዉ። መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በትብብር ተነስቶ ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ከስልጣን ማስወገድ አለበት።

ሌላዉ መግለጽ የምንፈልገዉ ጉዳይ የጎንደርን መሬት ለመከለል አጀንዳ ይዘዉ ባጀት ተመድቦላቸዉ ስለሚንቀሳቀሱ የክፉ ቀን ባንዳወች ነዉ። እነዚህ የዘረኛዉ ftድን ቅጥረኞች ወደመቀሌ ተመልምለዉ ሂደዉ አብዛኛወቹ የትግራይ ዝርያ የሆኑ እንዲሁም የጋብቻና የጥቅም ትስስር ያላቸዉ ከፍተኛ የብሄርተኝነት ፖለቲካ ስልጠና ለአለፉት 4 ዓመታት በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። በተለይ በሽሬ እንደስላሴ የቅማት የአንቀጽ 39 አቀንቃኞች እና በጣት የሚቆጠሩ የወያኔ ተላላኪዎች የወታደራዊ፤ የመረጃ እና ልዩ ኮማንድ ስልጠና እያካሄዱ ሲሆን አሁን የሚጠበቀዉ የቅማንትና አማራ መሬት ተከልሎ የሚከተሉት ሁኔታወች እስከሚከሰቱ  ነዉ።

በቅድሚያ በብዛት የትግራይ ካድሬወችና መኮንኖች የተሳተፉበት ክፍለጦር ማቋቋምና በሚፈጠረዉ አዲስ የቅማንት ቦታ ማሰማራት፤ ወያኔ አቀፍ አስተዳደር ማዋቀር እና ቀስበቀስ በመቆጣጠር የቅማት የተባለዉ መሬት እንደጋምቤላ እጣፈንታዉ በትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ሥር ማስገባት ነዉ። እንግዲህ የጎንደር ክፍለ ሃገር ታሪካዊ ሙሉ ባለቤት የሆነዉን የቅማንትና የአማራ ህዝብ ጎራ ለይቶ የኔ ያንተ አገር በሚል የእርስበርስ ብጥብጥን ለማነሳሳት የታሰበ የተለመደ የወያኔ ሰይጣናዊ ዕቅድ ነው።

ሌላዉ የወያኔ ዋና ሥራ ቅራኔ መፍጠር ነዉ፤ከፋፍሎ ቅራኒ መፍጠር የህልዉና ጉዳይ በመሆኑ፤ በሜዳ ግጦሽ,፣ በቤተ ክርስቲያን ቦታ ይገባኛል ፤ በወንዝ መስኖ የአካባቢዉ አርሶ አደር መስለዉ ተቀላቅለዉ ጠብን መጫር ይጀምሉ። ሁለቱን ህዝቦች በማናቆር ወያኔ ግምገማ አስቀምጦ የቅማት የተባለዉ የአናሳ አስተዳደር በ,ሚል ስበብ እንደቢሻንጉልና ጋምቤላ ሙሉ በሙሉ በወያኔ አስተዳደር ስር ይሆናል ማለት ነዉ። የወያኔ ተግባር አታሎ ቀምቶ የማትረፍ ስራ ነዉ። ለህዝብ የሚጠቅም ሳይሆን መጉዳት እና ታሪክ ማጥፋት በመሆኑ የመጨረሻዉ እርምጃ አማራም ቅማንትም  ተዳክመዉ፤ ተገፍተዉ ይፈናቀላሉ፣ ሱዳንንና ወያኔ 60% ጎንደርን ይቆጣጠራሉ።

የጎንደር/የአማራ ብሎም የመላዉ ኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ቁሞ መጠየቅ ያለበት

1ኛ) አማራና ቅማንትን በዘር ለመከለል የተቀናበረዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ሴራ በአስቸኳይ ይቁም

2ኛ) የሱዳን አንድ ክፍለ ጦር ወታደር ቋራ/ሽንፋ ላለፉት ሁለት ዓመታት በወረራ የቆ የዉጭ አገር ሠራዊት በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ምድር ለቆ ይዉጣ

3ኛ ) ወልቃይት ጠገዴ ፤ቃብቲያ ሁመራ/ጠለምት እራያ በጉልበት የተነጠቁ መሬቶች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲመልሱ።

4ኛ) ኮኖሬል ደመቀ ዘዉዱ፤ ዶክተር መራራ ጉዴና፤ አቶ በቀለ ገርባ አቶ እንዳርጋቸዉ ጽጌ ፤ አንዷለም አራጌ፤ንግስት ይርጋ፤ አስቴር ማሞ፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፤ተመስገን ደሳለኝ ፤ሰጠኝ አግባዉእና በአፈና የታሰሩ ከመቶ ሽህ በላይ የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ ያለ ምንም ቅድመሁኔታ በመላ አገሪቱ ወህኒቤቶች ይፈቱ፤

5ኛ) በጎንደር ፣ባህርዳርና በኦሮሚያ በሽወች የተሰዉት ወንድም እህቶቻችን ደም የታጠበ ወያኔ አይገዛንም በአስቸኳ ከስልጣን ይዉረድ የህዝብ መንግስት ይቋቋም።

LEAVE A REPLY